SlideShare a Scribd company logo
1 of 20
Download to read offline
ጣፋጭ

ዜና መፅሔት

ራዕይ፡ በቀጣይ ዕድገት ላይ የተመሰረተና በአለም ተወዳዳሪ የሆነ የስኳር ኢንዱስትሪ መፍጠር

ቅፅ 2. ቁጥር 2 -ታህሳስ 2006

www.etsugar.gov.et.com || www.facebook.com/etsugar

ኮርፖሬሽኑ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን ከተቀመጠው
የስኳር ልማት ንዑስ ዘርፍ ግብ 70 በመቶውን ማሣካት ይችላል
• የእቅድ ዘመኑን የስኳርና ተጓዳኝ ምርቶች ግብ ተደራሽነት የሚያመለክት ፍኖተ ካርታ (Roadmap) ተዘጋጀ
ስኳር ኮርፖሬሽን በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመኑ
ከሚገነባቸው የስኳር ፋብሪካዎች ውስጥ ሰባቱን በእቅድ ዘመኑ
መጨረሻ ድረስ ምርት በማስጀመር የዕቅዱን 70 በመቶ ማሣካት
የሚያስችለው ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡

በዚህ መሰረት በዚህ ዓመት ተንዳሆ 1 እንዲሁም በ2007 ዓ.ም ተንዳሆ
2፣ ኩራዝ 1፣ ከሰም፣ በለስ 1 እና 2 እና አርጆ ዲዴሳ ተጠናቀው ምርት
ይጀምራሉ፡፡ በሌላ በኩል ወልቃይት፣ በለስ 3 እና ኩራዝ 2 እና 3
በ2ኛው ምዕራፍ የዕቅድና ትራንስፎርሜሽን ዘመን የመጀመሪያዎቹ
ዓመታት ምርት ማምረት ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ »» ገጽ.3

የዓለም ኤድስ ቀን በአገር አቀፍ ደረጃ በመተሐራ ስኳር
ፋብሪካ ተከበረ

25 ኛው

ደረጃ በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ተከበረ፡፡
የዓለም ኤድስ ቀን “አንድም በበዓሉ ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፕሬዚዳንት
ሰው
በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ
እንዳይያዝ ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ፣ የጤና ጥበቃ
ኃላፊነታችንን በመወጣት የአገራችንን ሕዳሴ ሚኒስትሩ ዶክተር ከሰተብርሀን አድማሱ ፣
እናሳካ!” በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ
»» ገጽ.5

የሸንኮራ አገዳ አብቃይ ህብረት
ሥራ ማህበራት ከወንጂ ሸዋ
ስኳር ፋብሪካ ጋር ለጋራ
ጥቅም ለመስራት ተስማሙ
የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ እና የሸንኮራ
አገዳ አብቃይ አርሶ አደሮች ህብረት ሥራ
ማህበራት የጋራ ተጠቃሚነታቸውን
ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ
ከህዳር 7–14/2006ዓ.ም ውይይት
አካሂደዋል፡፡ በመጀመሪያው ዙር ከህዳር
7-13/2006 ዓ.ም ድረስ በነበረው
ጊዜ የውይይት መድረኮች የተካሄዱት
»» ገጽ.4

አቶ ሽፈራው ጃርሶ በበዓሉ ላይ ንግግር ሲያደርጉ

የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች የብሔር ብሐረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን በድምቀት አከበሩ
የስኳር ኮርፖሬሽን የስራ አመራሮችና
ሠራተኞች
ስምንተኛውን
የብሔር
ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን ህዳር 28
ቀን 2006 ዓ.ም በድምቀት አከበሩ፡፡
“ሕገ መንግስታችን ለሕዳሴያችን” በሚል
መሪ ቃል በተከበረው በዚህ በዓል የእንኳን
አደረሳችሁ
መልዕክት
ያስተላለፉት
የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር የኮርፖሬት
ሪፎርምና አቅም ግንባታ አማካሪ አቶ አደባባይ
በውስጥ ገፆች
የስኳር ልማት በሚካሄድባቸው
አካባቢዎች የሚገኙ ... ገጽ. 15

አባይ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ከመበታተን አደጋ
ወጥተው አንድ መሆን የቻሉት የቃል ኪዳን
ሰነዳቸው በሆነው ሕገ መንግስት አማካይነት
መሆኑን አስታውሰው ፣ ሕገ መንግስቱን
በማወቅና በማሳወቅ እንዲሁም እሴቶቹን
በመፈጸም ኃላፊነትን መወጣት ይገባል
ብለዋል፡፡
የኢፌዴሪ ሕገ መንግስት የሕዝቦችን በጋራ
አብሮ የመኖር በጎ ልምዶችን በማጠናከርና
»» ገጽ.15

የሳቡሬ ከተማ ከስኳር ልማቱ ተጠቃሚ
እየሆነች ነው...ገጽ. 8

አቶ አደባባይ አባይ

ጣና በለስ የተቀናጀ የስኳር ልማት
ፕሮጀክት ....ገጽ. 19

በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት :+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 A.A
Sugar_corp@ethionet.et | www.etsugar.gov.et | www.facebook.com/etsugar
ጣፋጭ ዜና መፅሄት

የዋና ዳይሬክተሩ መልዕክት

ክቡር አቶ ሽፈራው ጃርሶ
በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን
ዋና ዳይሬክተር

የአምስት ዓመቱ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን
ዕቅድ የግብርና ምርቶችን በዓይነትና በጥራት
የምናሣድግበት ብቻ ሣይሆን ከግብርና ወደ
ኢንዱሰትሪ የምናደርገውን መዋቅራዊ ሽግግርም
የምናሰፋበትና የምናፋጥንበት ጭምር ነው፡፡
ይህን መዋቅራዊ ሽግግር ተግባራዊ ለማድረግ
ከተያዙ ዕቅዶች መካከል የስኳር ልማት
ንዑስ ዘርፍ ዋንኛው ነው፡፡ ዘርፉ ግብርናን
ከኢንዱስትሪው ጋር በማገናኘት ሰፊ የሥራ
ዕድል የሚፈጥር፣ የግብርና ምርታማነትን
ለማጎልበት የሚያስችል፣ የቴክኖሎጂ ዕውቀትና
ክህሎት ለማሣደግ የሚያግዝ፣ የአገር ውስጥ

የስኳር ምርት ፍላጎት ከመሸፈን አልፎ ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሪ ለማስገኘት የሚያስችል
ነው፡፡ በተጓዳኝ በሚመረቱ ምርቶችም የአገሪቷን የኃይል አቅርቦት በመደገፍ፣ ኤታኖልን የመሳሰሉ
ከውጭ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚገቡ የነዳጅ ምርቶችን በመቀነስ እና ለሌሎች ኢንዱስትሪዎች
ግብዓት የሚሆኑ ምርቶችን በማምረት ዘርፉ ሊያበረክት የሚችለው አስተዋፅኦ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡
በቅርቡ የስኳር ልማት ንዑስ ዘርፍ ያለፉትን ሦስት ዓመታት አፈፃፀም ለማየትና በቀሪዎቹ የዕድገትና
የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ትግበራ ጊዜያት የት መድረስ እንደሚቻል ለመረዳት ባካሄድነው ግምገማ
ለዕቅድ ዘመኑ ከተቀመጠው ግብ 70 በመቶውን ማሣካት እንደምንችል አይተናል፡፡ በዚሁ መሠረት
አዳዲስ ከሚገነቡ ፋብሪካዎች ሰባቱን ማለትም ተንዳሆ አንድን በያዝነው ዓመት እንዲሁም
ተንዳሆ ሁለት፣ ኩራዝ አንድ፣ ከሰም፣ በለስ አንድና ሁለት እና አርጆ ዲዴሣ፣ በ2007 ዓ.ም.
ተጠናቀው ማምረት ይጀምራሉ፡፡ እነዚህ ወደ ማምረት የሚገቡ ፋብሪካዎች ከፍተኛ የማስፋፊያ
ሥራ ከተሰራላቸው ነባር ሦስት ፋብሪካዎች ጋር በድምሩ በ2007 መጨረሻ ከ1.5 ሚሊዮን ቶን
ያላነሰ ስኳር ማምረት የሚያስችሉን ይሆናሉ፡፡ በተመሣሣይ በተጓዳኝ የሚመረቱ ምርቶች መጠን፣
በልማት አካባቢዎቹ የሚካሄዱ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትና የመሠረተ ልማት ግንባታ፣
እንዲሁም የሥራ ዕድል ፈጠራና መሰል የልማት እንቅስቃሴዎች ጉልህ በሆነ ደረጃ ያድጋሉ፡፡
በቀጣዩ ዓመት መጨረሻ የምንደርስበት ግብም ሆነ ከዚያ ቀጥሎ ባሉ ቀጣይ ጊዜያት በስኳር
ልማት ዘርፍ ልናስመዘግብ የምናስበው ውጤት ከምንም በላይ ምርታማነታችንን በማሣደግ ላይ
የተመሠረተ ነው፡፡
ከዚህ አኳያ በሔክታር ከ1500 ኩንታል ያላነሰ የሸንኮራ ምርት ለማግኘት የሚያስችሉን የመሬት
እንክብካቤና የግብዓት አቅርቦት እንዲሁም የጥናትና የምርምር ሥራዎች ላይ አተኩረን እንሰራለን፡፡
የቴክኖሎጂ ዕውቀትና አጠቃቀማችንን በከፍተኛ ደረጃ ለማሻሻልም ትኩረት ሰጥተን እንንቀሳቀሳለን፡
፡ ጤንነቱ የተጠበቀ፣ ምርታማነቱ የላቀ፣ ሥነ-ምግባሩ የጎለበተ አምራች የሰው ኃይል በኢንዱስትሪው
ውስጥ በብዛት እንዲፈጠርም ልዩ ልዩ ተግባራትን እናከናውናለን፡፡ ኢንዱስትሪው ሠላማዊና
የተረጋጋ ሆኖ እንዲቀጥል ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ ተግባራትም ይከናወናሉ፡፡ የዚህ ሁሉ
ድምር ውጤት ከፍተኛ የስኳርና የተጓዳኝ ምርቶች በማምረት የአገሪቱን ኢኮኖሚ በከፍተኛ ደረጃ
በማሳደግ ህዝባችንን እና የዚህ ውጤት ተዋናይ የሆነውን ሠራተኛ የእድገቱ ተጠቃሚ ማድረግ
ነው፡፡ በእርግጥ ከፊታችን ያለው ትልቅ ኃላፊነት የሚጠይቅ ተልዕኮ ነው፡፡ የተቋሙ ሥራ አመራር
አባላትና ሠራተኞች እንዲሁም በተለያዩ የኮንትራት ሥራዎች ውስጥ የሚሣተፉ መንግሥታዊና
መንግሥታዊ ያልሆኑ ባለድርሻ አካላት ሁላችንም ልናሣካው የሚጠበቅብንን ትልቅ ተልዕኮ
የሚመጥን ምላሽ ለመስጠት በጋራ እንድንረባረብ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ፡፡

2
በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

ኮርፖሬሽኑ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን...
ኮርፖሬሽኑ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱን
የሶስት ዓመታት (2003 - 2005 ዓ.ም ) አፈጻጸም
በመፈተሽ በአምስት ዓመቱ የስኳር ልማት እቅድ
የት መድረስ እንደሚቻል በትክክል ለማወቅ
ባደረገው ግምገማ በአምስት አመቱ የእቅድ ዘመን
በስኳር ልማት ዘርፍ ከተቀመጠው የከፍተኛ
አማራጭ የግብ ስኬት 70 በመቶውን ማሣካት
እንደሚችል አረጋግጧል፡፡

የሚቻልበት ደረጃ ላይ የሚያደርስ ይሆናል፡፡
በአሁኑ ወቅት ኮርፖሬሽኑ አገሪቱ ስኳር ከውጭ
ለማስመጣት ታወጣ የነበረውን ከፍተኛ የውጭ
ምንዛሬ ማዳን የሚችልበት ደረጃ ላይ የደረሰ
ሲሆን እንዲያውም በ2007 ዓ.ም ወደ 658,200
ቶን ስኳር ወደ ውጭ በመላክ ከ376 ሚሊዮን
ዶላር በላይ ዓመታዊ የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት
አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡

አገሪቱ በስኳር ልማት ዘርፍ ያላትን ከፍተኛ እምቅ
አቅም በማልማት ተጠቃሚ ለመሆን በዕድገትና
ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አዳዲስ ፋብሪካዎችን
የመገንባትና የነባሮቹን አቅም በከፍተኛ ደረጃ
የማሣደግ ዕቅድ ተይዞ ነበር፡፡ ምንም ዓይነት
የመሠረተ ልማት አውታሮች ባልነበሩበት፣ ለዘርፉ
ልማት የሚውል በቂ ፋይናንስ በሌለበትና የዘርፉ
ልምድና የማስፈፀም አቅም ውስን በነበረበት ሁኔታ
ሥራው የተጀመረ ከመሆኑ አኳያ ሲታይ አሁን
የተደረሰበት ውጤት እጅግ ተስፋ ሰጪ ነው፡፡

በቀሪዎቹ
የትግበራ ጊዜያት የመስኖ ልማት
ግንባታን አጠናክሮ በመቀጠልና በፕሮጀክቶች
149,790 ሔክታር አገዳ በመትከል በአጠቃላይ
የፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች የአገዳ ሽፋንን
ከ204,000 ሄክታር በላይ ለማድረስ ጥረት
ይደረጋል፡፡
የማስፋፊያ ስራ በተጠናቀቀላቸው በነባር ስኳር
ፋብሪካዎችና በአዳዲስ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች
አማካኝነት በ2006 እና በ2007 ዓ.ም ከ92 ሺህ
በላይ ተጨማሪ የሥራ ዕድሎች ይፈጠራሉ፡
በመሆኑም ሥራው ሲጀመር በነበረው በዚህ ፡ የልማቱ ሥራ በሚካሔድባቸው አካባቢዎች
አስቸጋሪ ሁኔታ የከፍተኛውን የግብ ስኬት የሚገኘው ሕብረተሰብም በፕሮጀከቶቹ አማካኝነት
አማራጭ 70 በመቶ መድረስ ከተቻለ በቀጣይ ከሚፈጠሩ የስራ ዕድሎች በቀጥታና በተዘዋዋሪ
አጭር ሊባል በሚችል ጊዜ ውስጥ በስኳር ልማት ተጠቃሚ የሚሆንበት አቅጣጫም ተቀምጧል፡፡
ከዓለም ግንባር ቀደም ስኳር አምራች አገሮች ተርታ
መሰለፍ እንደሚቻል አሁን የተደረሰበት ውጤት ከስኳር ምርት በተጓዳኝ በእቅድ ዘመኑ መጨረሻ
አመላክቷል፡፡
ከስኳር ፋብሪካዎቹ 197 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ
ኃይል የማመንጨት አቅም ላይ እንደሚደረስ
ኮርፖሬሽኑ እያካሄዳቸው ካሉ የስኳር ፋብሪካ ይገመታል፡፡ ከዚህም ባሻገር በ2007 የኢታኖል
ግንባታዎች መካከል የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ምርትን ከ134 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ በማድረስ
የመጀመሪያ ምዕራፍ በማጠናቀቂያ ሂደት ላይ አገሪቱ ለነዳጅ የምታወጣውን ወጪ ለመቀነስ
የሚገኝ ሲሆን፣ በዚህ የበጀት ዓመት ወደ ማምረት ኮርፖሬሽኑ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡
ይሸጋገራል፡፡ የበለስ 1 እና 2፣ የኩራዝ 1፣ የተንዳሆ
2፣ የከሰምና የአርጆ ዲዴሳ ፋብሪካዎች ደግሞ ኮርፖሬሽኑ በ2006 እና በ2007 በቁጥር 3,265
በ2007 ማምረት ይጀምራሉ፡፡ በማስፋፊያ የመኖሪያ ቤት፣ የአገልግሎት መስጫና ተያያዥ
ፕሮጀክቶችም በኩል ወንጂ ሸዋና ፊንጫአ ስኳር ግንባታዎችን አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃትም
ፋብሪካዎች ተጠናቀው ተጨማሪ ምርት በመስጠት በመረባረብ ላይ ነው፡፡
ላይ ናቸው፡፡
በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የስኳርና
በእስካሁን የልማት ጥረት ዓመታዊ የሀገር ውስጥ ተጓዳኝ ምርቶች ግብ ተደራሽነት ፍኖተ ካርታ
የስኳር ምርት በ2005 መጨረሻ ከነበረበት 232 (Road Map) በጥቅምት ወር ተዘጋጅቶ በሥራ
ሺህ ቶን ተከታታይ ዕድገት በማስመዝገብ በ2007 ላይ ውሏል፡፡ ፍኖተ ካርታው በስኳርና ተጓዳኝ
መጨረሻ ከ1 ሚሊዮን 585 ሺህ ቶን በላይ ምርቶች ኢንዱስትሪ ልማት ንዑስ ዘርፍ ውስጥ
እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡ ይህም የአገር ውስጥ በ2006 እና በ2007 ዓ.ም ተፈጻሚ የሚሆኑ ዋና
ፍጆታ ከመሸፈን አልፎ ምርቱን ወደ ውጭ መላክ ዋና ግቦችን አካቷል፡፡

3
ጣ የሸንኮራ አገዳሄ ት
ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ አብቃይ
በምስራቅ ሸዋና አርሲ ዞኖች በሚገኙና
የሸንኮራ አገዳ ልማቱ በሚካሄድባቸው
ወረዳዎችና
ቀበሌዎች
ከተውጣጡ
በየደረጃው ከሚገኙ አመራር አካላት፣
የሸንኮራ አገዳ አብቃይ አርሶ አደሮችና
ህብረት ሥራ ማህበራት ተወካዮች ጋር
ነው፡፡
ህዳር 14 /2006 ዓ.ም. በአዳማ ገልማ
አባገዳ የስብሰባ አዳራሽ ለስድስት ቀናት
በተለያዩ ደረጃዎች ሲካሄድ የቆዩ ውይይቶች
የማጠቃለያ መድረክ የተዘጋጀ ሲሆን፣
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ርዕሰ
መስተዳድርና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ
ክቡር አቶ አብዱላዚዝ መሐመድ፣ የክልሉ
ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት፣ የፌዴራል ህብረት
ስራና ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች
የስራ ኃላፊዎች፣ የስኳር ኮርፖሬሽን የስራ
ኃላፊዎች፣ የሸንኮራ አገዳ አብቃይ አርሶ
አደር ማህበራት አመራሮች፣ ከየአካባቢዎቹ
የመጡ አርሶ አደሮች፣ የምሥራቅ ሸዋና
የአርሲ ዞኖች አስተዳዳሪዎችና ሌሎች
የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የአዳማ፣
የቦሰትና የዶዶታ ወረዳዎች አመራሮችና
ሌሎች የሚመለከታቸው 581 ተሳታፊዎች
በማጠቃለያ መድረኩ ላይ ተገኝተዋል፡፡
የስኳር ኮርፖሬሽን የህዝብ አደረጃጀት
ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳመነ
ዳሮታ በውይይቱ ላይ “በወንጂ/ሸዋ ስኳር
ፋብሪካ እና በሸንኮራ አገዳ አብቃይ አርሶ
አደር ማህበራት (አውትግሮወርስ) መካከል
የሚታየው የልማት አፈጻጸም፣ ተግዳሮቶችና
ኪራይ ሰብሳቢነት” በሚል ርእስ የመወያያ
ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡
አቶ ዳመነ ባቀረቡት ጽሁፍ የአገዳ መሸጫ
ዋጋ ሳይሻሻል መቆየቱ፣ የተሟላ የመሰረተ
ልማት እጥረት፣ ለሸንኮራ አገዳ እድገት
የሚበጁ እንክብካቤዎች ወቅታቸውንና
ጥራታቸውን ጠብቀው ባለማከናወናቸው
ምክንያት የሚከሰት የምርታማነት ማነስ፣
ከልማቱ ጋር የሚጣጣም የስራ ባህል
አለመኖር፣ በአንዳንድ ማሳዎች ላይ ወቅቱን
ጠብቆ መሬቱን አለማዘጋጀት፣ በቂ የሆነ
የመስኖ ውኃ አለማቅረብ፣ የመድን ሽፋን

4

ህብረት ሥራ ማህበራት ከወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ጋር ...
አለመኖርና ሌሎችንም ተያያዥ ችግሮች
ጠቅሰዋል፡፡
በተጨማሪም በዩኒየን አመራር፣ በመሰረታዊ
ማህበራት
አመራርና
በፋብሪካው
በኩል የሚንጸባረቁ የኪራይ ሰብሳቢነት
አመለካከትና ተግባራት እንዲሁም የአሰራርና
የአደረጃጀት
ክፍተትም
እንደችግር
ተነስተዋል፡፡
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በጽሁፋቸው
ማጠቃለያ በመፍትሔነት ከጠቀሱዋቸው
ሐሳቦች መካከል የኪራይ ሰብሳቢነት ትግሉን
በቀጣይነት አጠናክሮ መቀጠልና ግልጽነት
ያለው አሰራርና ድጋፍ አሰጣጥ ማስፈን፣
የአቅም ግንባታ ስራዎችን ማጠናከር፣
አሰራርን ማሻሻል፣ የመድን ሽፋን እንዲኖር
ማድረግ፣ የባለድርሻ አካላት ድጋፍና
ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር የሚሉትና
ሌሎችም ይገኙበታል፡፡
በውይይቱ ወቅት የሸንኮራ አገዳ አብቃይ
አርሶ አደር ማህበራት አመራሮችና አባላት
መፍትሔ ያሻቸዋል ያሉዋቸውን ጉዳዮች
አንስተዋል፡፡ ከነዚህም መካከል ለፋብሪካው
ለሚያቀርቡት የሸንኮራ አገዳ ምርት ዋጋ
ይሻሻል፣ ከመስኖና ከሌሎች የምርት
ግብአቶች አቅርቦት ጋር በተያያዘ ፈጣን
አገልግሎት የሚሰጥበት መንገድ ይመቻች፣
በማቆያ የተያዙ መሬቶች ቶሎ ወደ ልማት
ይግቡ የሚሉና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችም
ይገኙበታል፡፡
የኮርፖሬሽኑ
ተወካዮች
የውይይት
መድረኩ በሸንኮራ አገዳ አብቃይ አርሶ
አደሮች ማህበራትና ፋብሪካው እንደ
ችግር የሚያነሷቸውን ጉዳዮች በመለየት
ሁሉንም ተጠቃሚ በሚያደርግ አኳኋን
ለማስተናገድ የተመቻቸ መሆኑን ገልፀዋል፡
፡ ስኳር ለማምረት ብዙ ግብዓቶች ጥቅም
ላይ እንደሚውሉ የገለጹት የኮርፖሬሽኑ
ተወካዮች ይህንን ታሣቢ ያደረገ የዋጋ
ድርድር ለማካሄድ ጭምር መድረኩ
መመቻቸቱን አስረድተዋል፡፡
በአገልግሎት አቅርቦት ረገድ አሉ የተባሉ

ችግሮችን ለመፍታትም ፋብሪካው ያላሰለሰ
ጥረት
እንደሚያደርግ
አብራርተው
በተመሣሣይ ከአርሶ አደሮች በኩል
ከምርታማነትና ፋብሪካውን እንደ አገርና
እንደራሣቸው ሐብት አድርጎ በመቁጠር ረገድ
ያሉ የአመለካከት ችግሮች እንዲስተካከሉ
አሳስበዋል፡፡
በቀጣይም
ፋብሪካውና
ማህበራቱ በመደበኛ ሁኔታ በመወያየት
ሁለቱንም አካላት ተጠቃሚ የሚያደርግ
አቅጣጫን መከተልና ለጋራ ልማት አብረው
መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
መድረኩን የመሩት የኦሮሚያ ክልላዊ
መንግሥት ም/ርዕሰ መስተዳድሩ በሰጡት
የማጠቃለያ ሐሣብ በአገሪቱ ልማት
ውስጥ ትልቅ ስፍራ ላለው የስኳር ልማት
መሳካት የምስራቅ ሸዋና የአርሲ ዞኖችና
የየወረዳዎቹ
አመራሮች
እንዲሁም
የፋብሪካውና የማህበራትና የዩኒየኖች
አመራሮችና
ሰራተኞች
ተቀናጅተው
እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡ ም/ርዕሰ መስተዳድሩ
ህብረተሰቡም ፋብሪካው እራሱንም ሆነ
አገሪቱን በከፍተኛ ደረጃ የሚጠቅም መሆኑን
ተረድቶ የባለቤትነት ስሜትን እንዲያዳብር
በማሳሰብ የሁለቱ ግንኙነት በግልጽነትና
በፈጣን አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተመሰረተ
መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡ ለዚህም
ስኬት የውይይት መድረኮች በመደበኛነት
ተጠናክረው እንደሚካሄዱ ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም
በየደረጃው
የሚገኙ
አመራሮች፣ የስራ ኃላፊዎች፣ የሸንኮራ አገዳ
አብቃይ አርሶ አደር ማህበራት አመራርና
አባላት፣ የዩኒየን አመራሮችና ሰራተኞች
እንዲሁም የፋብሪካው አመራሮችና ሰራተኞች
ተወካዮች ሁሉንም ተጠቃሚ በሚያደርግ
መልኩ ተቀናጅተው ለመስራት ባለ ስድስት
ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል፡፡
በአቋም መግለጫቸውም የስኳር ልማቱ የአርሶ
አደሩን ኑሮ ለመለወጥና ለሀገር ልማትም
ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው በመገንዘብ
ለውጤታማነቱ እጅ ለእጅ ተያያይዘው
ለመስራትና የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን
በውይይት እየፈቱ ለመሄድ የየበኩላቸውን
ድርሻ እንደሚወጡ አረጋግጠዋል፡፡

በማህበራቱና በፋብሪካው መካከል ውይይት በተደረገበት ወቅት
በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

የዓለም ኤድስ ቀን በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ በተከበረበት ወቅት

የዓለም ኤድስ ቀን በአገር አቀፍ ደረጃ በመተሐራ...
በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና
ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ፣ የኦሮሚያ
ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ
አብድላዚዝ መሐመድና ሌሎች ተጋባዥ
እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች ለሚመሩ
ስኳር ኮርፖሬሽንን ለመሳሰሉ ተቋማት
ኤች.አይ.ቪ
ኤድስን
መከላከልና
መቆጣጠር ተልዕኮን ከማሳካት ጋር ጥብቅ
ቁርኝት አለው ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሙላቱ በበዓሉ ላይ ባደረጉት
ንግግር በመላ አገሪቱ በተፈጠሩ
በብዚ ሺ የሚቆጠሩ አምራች ኃይሎች
በሚንቀሳቀሱባቸው ታላላቅ የልማትና
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ልዩ
ትኩረት በማድረግ የኤች.አይ.ቪ ኤድስ
ስርጭትን መግታት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ
የሚገኝባቸውን 2100 ሠራተኞችንና
በበሽታው ወላጆቻቸውን ያጡ ሕጻናትን
ከመደገፍና ከመንከባከብ በተጓዳኝ
የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የተለያዩ
የመከላከል ተግባራትን በማከናወን ላይ
እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ የሚገኝባቸው
ወገኖች
የጸረ-ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ
መድኃኒት አግኝተው አምራች ኃይሎች
እንዲሆኑና በአገራቸው የልማትና የእድገት
ጉዞ ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ
እንዲያበረክቱ ማገዝና መርዳት አስፈላጊ
ነውም ብለዋል ፕሬዚዳንት ሙላቱ፡፡

ከዚህ
በተጨማሪ
በመከላከልና
በእንክብካቤ ስራው ውስጥ ጉልህ ሚና
የሚጫወት የኤች.አይ.ቪ ግብረ ኃይል
መቋቋሙንና ከተቋሙ አመታዊ በጀት
ላይ ሁለት በመቶ የሚሆነው ለዚሁ ስራ
እንዲውል መመደቡንም አብራርተዋል፡፡

በዓሉ የተከበረበት የመተሐራ ስኳር
ፋብሪካን በመሳሰሉና በመገንባት ላይ
ባሉት ታላላቅ ፕሮጀክቶችና በተለያዩ
የልማት ተቋሞች በመስራት ላይ የሚገኙ
ወጣቶች ከኤች.አይ.ቪ./ኤድስ ራሳቸውን
መጠበቅ ቀዳሚ ተግባራቸው ሊሆን
እንደሚገባ ፕሬዚዳንቱ አሳስበዋል፡፡

በእስካሁኑ
ጅምር
የመከላከል፣
የመንከባከብና
ግንዛቤ
የመፍጠር
ስራዎች አበረታች ውጤቶች ቢመዘገቡም
የስኳር ልማት ዘርፉ ካለው ተጋላጭነትና
የተያዘውን እቅድ በአጭር ጊዜ ለማሳካት
ከፍተኛ ጥረት የሚጠይቅ ከመሆኑ አንጻር
ኮርፖሬሽኑ የበለጠ መስራት የሚጠበቅበት
መሆኑንም አቶ ሽፈራው ጠቁመዋል፡፡

በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን
ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ
በበኩላቸው ከስራቸው ባሕሪ የተነሳ
በርካታ የሰው ኃይል የሚሰማሩባቸውን

የዓለም ኤድስ ቀን በመተሐራ ስኳር
ፋብሪካ መከበሩ ኮርፖሬሽኑ የቫይረሱን
ስርጭት በመግታት ረገድ የተለየ ኃላፊነት
እንዲሸከም የሚያደርግ መሆኑን የገለጹት

ዋና ዳይሬክተሩ ለዚህም በዋና መስሪያ ቤት
፣ በፋብሪካዎችና በፕሮጀክቶች የተሰማሩ
ሰራተኞች የቫይረሱን ስርጭት በመከላከል
በስኳር ልማት ዘርፍ የተቀመጡ የልማት
ግቦችን ለማሳካት በበለጠ ቁርጠኝነት
እንዲነሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር
ከሰተብርሀን
አድማሱ
በበኩላቸው
ኢትዮጵያ ኤች.አይ.ቪ./ኤድስን በመከላከል
ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገቡ ከሚገኙ 16
የአፍሪካ አገሮች መካከል ግንባር ቀደም
መሆን መቻሏን አስታውቀዋል፡፡
በቀጣይም ሕዝብ በብዛት በሚገኝባቸው
የታላላቅ
ፕሮጀክቶች
ግንባታ
በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የተጠናከረ
የመከላከል ስራ እንደሚሰራ ይፋ
አድርገዋል፡፡
ኢትዮጵያ በኤች.አይ.ቪ የሚያዙ ሰዎችን
ቁጥር በ90 በመቶ እንዲሁም በቫይረሱ
ምክንያት ይደርስ የነበረውን ሞትና ጉዳት
ከ54 በመቶ በላይ መቀነስ መቻሏ በበዓሉ
ላይ ይፋ ተደርጓል፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ በዓሉ የተከበረበት
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ባቋቋመው አንድ
ሆስፒታል ፣ ሁለት ፖሊና አራት ሳተላይት
ክሊኒኮች
አማካይነት
ለፋብሪካው
ሰራተኞች ፣ ቤተሰቦቻቸውና ለአካባቢው
ነዋሪ ሕብረተሰብ የኤች.አይ.ቪ. ኤድስ
መከላከልና መቆጣጠር ስራ በመስራት ላይ
ይገኛል፡፡
5
ጣፋጭ ዜና መፅሄት

አዲሱ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብካ

የወንጂ ሸዋና የፊንጫአ ስኳር
ፋብሪካዎች በከፍተኛ የማምረት
አቅም ሥራ ጀመሩ
የማስፋፊያ
ሥራቸው
የተጠናቀቀው
የወንጂ ሸዋና የፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካዎች
ከጥቅምት ወር 2006ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ
በተሳካ ሁኔታ ሥራ ጀመሩ፡፡ የተካሄደው
የማስፋፊያ ሥራ የፋብሪካዎቹን የማምረት
አቅም በከፍተኛ ደረጃ ያሳድገዋል፡፡
የማስፋፊያ ፕሮጀክት ስራው የተጠናቀቀው
የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ የማምረት አቅሙን
በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ ከጥቅምት
10/2006 ዓ.ም ጀምሮ እያመረተ ነው፡፡
ፋብሪካው በ2006 በጀት ዓመት 2 ሚሊዮን
ኩንታል ስኳር ያመርታል ተብሎ የሚጠበቅ
ሲሆን፣ ይህ የምርት መጠን በ2005 በጀት
ዓመት ከተገኘው ምርት ጋር ሲነጻጸር የ900
ሺህ ኩንታል ልዩነት ይኖረዋል፡፡
ፋብሪካው በሂደት በሙሉ አቅሙ ማምረት
ሲጀምር በአመት ወደ 2 ሚሊዮን 700
ሺህ ኩንታል ስኳር ያመርታል ተብሎ
ይጠበቃል፡፡
በተመሳሳይ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ
6

ዕድሜ አገልግለው ስኳር ማምረት ባቆሙት
ነባሮቹ የወንጂ እና የሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች
ምትክ በተከናወነ የማስፋፊያ ፕሮጀክት
ግንባታው የተጠናቀቀው አዲሱ ዘመናዊ
የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ከጥቅምት
22/2006 ዓ.ም ጀምሮ ስኳር ማምረት
ጀምሯል፡፡
በ2005ዓ.ም መጨረሻ የሙከራ ምርት
ያካሄደው ይህ ፋብሪካ በያዝነው በጀት
ዓመት ከ950 ሺህ ኩንታል በላይ ስኳር
እንዲያመርት የታቀደ ሲሆን፣ ለምርቱ
የሚሆን በቂ የሸንኮራ አገዳና ሌሎች
አስፈላጊ ግብዓቶች ዝግጁ ሆነዋል፡፡

በሌላ በኩል በያዝነው በጀት ዓመት
1 ሚሊዮን 300 ሺህ ኩንታል ስኳር
እንደሚያመርት የሚጠበቀው የመተሃራ
ስኳር ፋብሪካ ስራ የጀመረ ሲሆን፣
የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታው በመጠናቀቅ
ላይ የሚገኘው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካም
በያዝነው በጀት ዓመት ምርት ይጀምራል
ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተጠቀሱት አራት የስኳር ፋብሪካዎች
በበጀት ዓመቱ ከ5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ
ስኳር ለማምረት የታቀደ ሲሆን፣ ይህም
ከአምናው ምርት ጋር ሲነጻጸር ከእጥፍ በላይ
ይሆናል፡፡ በዘርፉ ዘንድሮ የሚገኘው ምርት
የአገር ውስጥ የስኳር ፍላጎትን ከማሟላት
አሮጌዎቹ የወንጂ እና የሸዋ ስኳር ባለፈ ምርቱን ከውጭ ለማስገባት ይወጣ
ፋብሪካዎች በዓመት 750 ሺህ ኩንታል የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ሙሉ በሙሉ
ስኳር ያመርቱ የነበረ ሲሆን፣ በምትካቸው ያስቀራል፡፡
የተገነባው አዲሱ ፋብሪካ የመጀመሪያ
ምዕራፉ ብቻ በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምር የፋብሪካዎቹ የማምረት አቅም እንዲያድግና
በዓመት ከ1 ሚሊዮን 460 ሺህ ኩንታል የአመቱ የማምረት ተግባር ውጤታማ በሆነ
በላይ ስኳር የማምረት አቅም ይኖረዋል፡፡
መልኩ እንዲጀመር አመራሮችና ሠራተኞች
ሰፊ ርብርብ አድርገዋል፡፡
በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ጎበኙ

ሰራተኞቹ በግድቡ የግንባታ ሂደትና በተመለከቱት ነገር ደስተኛ ሆነዋል

የስኳር ኮርፖሬሽን ሠራተኞች “ከስኳር
ልማቱ ጎን ለጎን ለግድቡ ስኬት እንተጋለን!”
የሚል መሪ ቃል አንግበው በሁለት ዙሮች
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን
ጎበኙ፡፡
ሠራተኞቹ የኮርፖሬሽኑ የማህበራዊ ጉዳዮች
በሚያስተባብረው የአገርህን እወቅ ክበብ
አማካኝነት ግድቡ በሚገነባበት ቤኒሻንጉል
ጉሙዝ ክልል ጉባ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ
ተገኝተው ጉብኝት ያካሄዱት ጥቅምት 4 እና
ህዳር 9 ቀን 2006 ዓ.ም ነው፡፡
በመጀመሪያው ዙር 41 የኮርፖሬሽኑ
ሠራተኞች ከጥቅምት 2 ቀን 2006
ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ቀናት ግንባታው
በሚካሄድበት ስፍራ ጉብኝት ያደረጉ
ሲሆን፣ ከህዳር 9 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ
በተደረገው የሁለተኛው ዙር ጉብኝት ደግሞ
35 ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል ፡፡

በሁለቱም ዙሮች ግድቡ ወደሚገነባበት
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ
ላመሩት የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ስለ
ግድቡ ግንባታና ተያያዥ ጉዳዮች በከፍተኛ
የፕሮጀክቱ ባለሙያዎች በአዳራሽ ውስጥና
በመስክ ጉብኝት ሰፊ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡
በጉብኝቶቹ ወቅት በሥራ ምክንያት
በግንባታው ስፍራ መገኘት ያልቻሉት
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት
ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው
በቀለ ለኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ባስተላለፉት
የጽሁፍ መልዕክት “በቅድሚያ የራሳችሁን
ፕሮጀክት ስለጎበኛችሁ ላመሰግናችሁ
እወዳለሁ፡፡ በተመለከታችሁት ሁሉ ደስተኛ
እንደሆናችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በቀጣይ
ሁላችንም በከፍተኛ የአገር ፍቅር እጅ
ለእጅ በመያያዝና የተጀመረውን የልማት
ጉዞ ይበልጥ በማስቀጠል በኢኮኖሚ
የበለጸገች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ
በየተሰማራንበት የስራ መስክ ሁሉ ጠንክረን

መስራት ይጠበቅብናል ” ብለዋል፡፡
የግድቡን ግንባታ አስመልክቶ አንዳንድ
ያነጋገርናቸው ተጓዦች በሰጡን አስተያየት
በቴሌቪዥን መስኮት ብቻ ይመለከቱት
የነበረውን የግድቡን ሥራ በአካል ተገኝተው
መመልከታቸው የበለጠ የባለቤትነት
ስሜትና በቁጭት የመስራት ተነሳሽነትን
እንደፈጠረላቸው ገልጸው፣ ለግንባታው
ስኬት የጀመሩትን አስተዋጽኦ አጠናክረው
እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ከግድቡ በተጨማሪ
በአሶሳ ከተማ የሚገኙትን የሼህ ሆጀሌ
አልሃሰን የችሎት አዳራሽና የመቃብር ስፍራ
ጎብኝተዋል፡፡
በሦስት ዙሮች ተከፍሎ በመካሄድ ላይ
በሚገኘው የጉብኝት መርሐ ግብር
ለሦስተኛው ዙር ጉዞ ቅድመ ዝግጅት
በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡
»» ገጽ.8
7
ጣፋጭ ዜና መፅሄት

የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች...
ወደ ታላቁ የህዳሴ ግድብ
የጉዞ መርሃ ግብሩን ያዘጋጀው
የኮርፖሬሽኑ የአገርህን እወቅ
ክበብ ጥቅምት 23 ቀን 2005 ዓ.ም
ተቋቁሞ እስካሁን 117 አባላትን
ያቀፈ ሲሆን፣ ዓላማው ሠራተኞችን
ከማዝናናትና ግንዛቤ ከማስጨበጥ
ባለፈ መንግሥት በሚያካሂደው
ዘላቂ ልማት ላይ የበኩላቸውን
አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ማስቻል
ነው፡፡
በተመሳሳይ ዜና የፊንጫአ ስኳር
ፋብሪካ 39 ሠራተኞች፣ የጣና
በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት 300
ሠራተኞች እንዲሁም

የሳቡሬ ከተማ ከስኳር ልማቱ
ተጠቃሚ እየሆነች ነው
ስያሜዋን ከአንድ ፈረንሳዊ
ባለሀብት የወረሰችው የሳቡሬ
ከተማ የስኳር ልማቱን ተከትሎ
ከተዘረጉ መሠረተ ልማቶች
ተጠቃሚ መሆኗ ተገለጸ፡፡
በ1904 ዓ.ም እንደተቆረቆረች
የሚነገርላት
ይህች
ከተማ
የከሠም ስኳር ልማት ፕሮጀክትን
ተከትለው በተዘረጉ የመንገድ ፣
የተንቀሳቃሽ ስልክ፣ የገመድ አልባ
የብሮድባንድ ኢንተርኔትና የ24
ሰአት የመብራት አገልግሎቶች
ተጠቃሚ መሆን ችላለች፡፡
ከተማዋ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ
ለከሰም ስኳር ልማት ተብለው
በተዘረጉ የተለያዩ የመሠረተ
ልማት ስራዎች ተጠቃሚ መሆኗ
ለእድገቷ አስተዋጽዖ በማበርከት
ላይ እንደሚገኝ ተመልክቷል፡፡

የፊንጫአ ሰራተኞች በጉዞ ላይ

የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ 42
ሠራተኞች የታላቁ የኢትዮጵያ
ህዳሴ ግድብ የሥራ እቅስቃሴን
ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ ስለ ግድቡ
ፕሮጀክት አጠቃላይ እንቅስቃሴ
በመረዳታቸው
መደሰታቸውን
የገለጹት ሠራተኞቹ ለፕሮጀክቱ
የሚያደርጉትን ሁለንተናዊ ድጋፍ
አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል
ገብተዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር በተሰማሩበት
ዘርፍ ተልዕኮአቸውን በላቀ ሁኔታ
በመፈጸም አገሪቱ ወዳለመችው
የእድገት ደረጃ እንድትደርስ
በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ
የራሳቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት
ዝግጁነታቸውን ገልጸዋል፡፡

የአትክልትና ፍራፍሬ ልማትን ተከትላ የተመሠረተችውና
በኋላም የላይኛው አዋሽ አግሮ ኢንዱስትሪ የአትክልትና
ፍራፍሬ ልማት ሳቢያ የተስፋፋችው ሳቡሬ የገጠር
ከተማ ስትሆን ለበርካታ አመታት በቂ የማህበራዊ
አገልግሎት መስጫ ተቋማት አልነበሯትም፡፡
ከተማዋ የዘመናዊ የግንኙነት መረቦች ተጠቃሚ መሆኗ
እንደ ዳግም ልደት እንደሚቆጠርና በቀጣይ በፍጥነት
እድገት ለማስመዝገብ በምታደርገው ጥረት ውስጥ
ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንደሚኖረው የከሰም ስኳር
ልማት ፕሮጀክት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል የላከልን ዘገባ
አመልክቷል፡፡

በአንድ ቀን ከ 74 ሄክታር በላይ የሸንኮራ አገዳ ዘር
ተተከለ
በጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት
በሰራተኞች በተደረገ የተቀናጀ ንቅናቄ
በአንድ ቀን 74 ነጥብ 8 ሄክታር መሬት
በሸንኮራ አገዳ ዘር መሸፈኑ ተገለጸ፡፡

በመከፋፈሉና ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ
ዝግጅቶችን በማድረጉ ሰራተኛው በእለቱ
በተከላ ስራው ላይ ብቻ እንዲያተኩር ተደርጎ
ተፈላጊው ውጤት ሊገኝ ችሏል፡፡

በአገዳ ተከላ የንቅናቄ እቅድ ዙሪያ
የፕሮጀክቱ አመራር ከሰራተኛው ጋር
ባደረገው እንቅስቃሴ “ሁሉም መንገዶች ወደ
በለስ አገዳ ተከላ ያመራሉ!” በሚል መሪ
ቃል ወደ ተግባር ተገብቶ አበረታች ውጤት
መመዝገቡን የፕሮጀክቱ የህዝብ ግንኙነት
ክፍል ያደረሰን መረጃ ያመለክታል ፡፡

ለስራው የሚያስፈልገውን ተጨማሪ የሰው
ኃይል ከአማራና ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች
ከማቅረብ በተጨማሪ የአገዳ አቅርቦት
ችግር እንዳይኖር ያሉትን የፕሮጀክቱንና
በኪራይ የተገኙትን ተሽከርካሪዎች በአግባቡ
መጠቀም በመቻሉ እቅዱ ከግብ ደርሷል፡፡
በሌላ በኩል ሁኔታውን በቅርብ ይከታተል
የነበረው ከ3ዐዐዐ በላይ የሚሆን የጃዊ
ወረዳ ህዝብ ፣ የንግዱ ማህበረሰብና
የወረዳው የፖሊስ አባላት የሰራተኛውን
ሞራልና መነሳሳት በመደገፍ የሁለት ቀናት
የአገዳ ተከላ ዘመቻ ሥራ ማከናወናቸውን
የፕሮጀክቱ የህዝብ ግንኙነት ክፍል የላከው
መረጃ ያመለክታል ፡፡

የልማት ቡድኖችን በአራት የዞን ጽ/ቤቶች
ከፋፍሎ ስራን ቆጥሮ በመስጠትና በቡድኖቹ
መካከል ከፍተኛ የሆነ የሥራ ውድድር
መንፈስ በመፍጠር ውጤቱ ሊገኝ መቻሉን
ነው መረጃው የጠቆመው፡፡
የፕሮጀክቱ የአመራር ኮሚቴ ወረዳዎችን

8
በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

በላይ መድቦ እርጅና የተጫናቸው ማሽነሪዎች
እንዲሻሻሉና ለጥገና የሚያስፈልጉ ግብዓቶችም
በወቅቱ ከውጭ ሀገሮች እንዲገቡ በመደረጉ
ለጥገናው መፋጠን ከፍተኛ አስተዋጽኦ
አበርክቷል፡፡

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ
አጠቃላይ እድሳት በስኬት
ተጠናቀቀ
ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦለት
ሲከናወን የቆየው የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ
አጠቃላይ የእድሳት ሥራ ከተቀመጠለት
ዕቅድ አስቀድሞ በስኬት ተጠናቀቀ፡፡
የፋብሪካው ሠራተኞች ጥቅምት 29
ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ባካሄዱት የሦስት
ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ላይ
እደተመለከተው በስኳር ኮርፖሬሽን፣
በፋብሪካው አመራሮችና አጠቃላይ
ሠራተኞች በተደረገው ከፍተኛ ርብርብ
ለ14 ሳምንታት ሲካሄድ የቆየው ጥገና
በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቆ ስኳር ማምረት
ተጀምሯል፡፡

ፋብሪካውን ለማደስ በተካሄዱ የቅድመ
ዝግጅት ሥራዎችና ለሠራተኛው
በአመለካከት፣ በመልካም ግንኙነትና በቡድን
ግንባታ በተሰጡ ሥልጠናዎች በአመራሩ
እንዲሁም በአጠቃላይ ሠራተኛው ዘንድ
የባለቤትነት፣ የቁጭት፣ የተነሳሽነትና
የቁርጠኝነት ስሜቶች በመፈጠራቸው
በጥገናው ሂደት ላይ የታየው ርብርብ እጅግ
ከፍተኛ እንዲሆን አስችሎታል፡፡
የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘነበ
ይማም በግምገማው ወቅት እንደገለጹት
መንግስት ለፋብሪካው እድሳትና ጥገና
በሰጠው ልዩ ትኩረት ከ4ዐዐ ሚሊዮን ብር

ፋብሪካው ከቀድሞ በተለየ ሁኔታ እንዲጠገን
መደረጉን የገለጹት ዋና ሥራ አስኪያጁ በስራው
ላይ በተለይም ሠራተኛው ለተጫወተው
ከፍተኛ ሚና ታላቅ ክብር የሚገባው መሆኑን
ተናግረዋል፡፡
በጥገናው ላይ መላው ሰራተኛ ለ14 ሳምንታት
ያህል ከመደበኛ ስራው ውጭ በየዕለቱ ተጨማሪ
የአንድ ሰዓት ነጻ አስተዋጽኦ ያበረከተ ሲሆን
በዚህም ሰራተኛው 4.5 ሚሊዮን ብር ወጪ
ማዳኑ ታውቋል፡፤
በግምገማው ላይ የተሳተፉት ሠራተኞች
በበኩላቸው በጥገና ሂደቱ ከመንግሥት ጀምሮ
በተዋረድ እስከ ፋብሪካው ከፍተኛ አመራሮች
ድረስ የተሰጠው የቅርብ ድጋፍና ክትትል
ለስኬት እንዳበቃቸው ተናግረዋል፡፡
እንደ ተሳታፊዎቹ አስተያየት ቁርጠኛ
የለውጥ አመራር በመኖሩና ቀደም ሲል
የነበሩ የአመለካከት ክፍተቶች እየተለወጡ
በመሆናቸው ውጤታማ ተቋማዊ ለውጦችን
መመልከት ተችሏል፡፡
የለውጥ ንቅናቄው በፋብሪካ ብቻ ሳይወሰን
በመኖሪያ አካባቢዎችም ጭምር በመሆኑ
ከፍተኛ የባለቤትነት ስሜት በመፈጠሩ
በቀጣይም የተጀመረውን ተቋማዊ ለውጥ
አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተሳታፊዎቹ
መግለጻቸውን የዘገበው የመተሐራ ስኳር
ፋብሪካ ሕዝብ አደረጃጀት፣ ሕዝብ ግንኙነትና
ማህበራዊ ጉዳዮች ክፍል ነው፡፡

ፕሮጀክቱ አመታዊ እቅዱን ለማሳካት እየሰራ ነው
የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የ2006 የበጀት
አመት እቅድ ትግበራ ዝግጅቱን ከቀሪ የእድገትና
ትራንስፎርሜሽን እቅድ ጋር የተጣጣመ ለማድረግ እየሰራ
መሆኑን ገለጸ፡፡
የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሲሳይ
አስራት እንደገለጹት የፕሮጀክቱ የፋብሪካ ግንባታ ስራ
እየተጠናቀቀ የሚገኝ በመሆኑ ከዴዴሳ ወንዝ ውሃ በቀጥታ
በመሳብ እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ ስድስት ሺ ሄክታር መሬት
ላይ ሸንኮራ አገዳ ለመትከልና ፋብሪካውን በማሟሸት

ምርት ለመጀመር እየሰራን ነው ብለዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ይህን እቅዱን ለማሳካት በሁለት ሺ ሄክታር
መሬት ላይ ሸንኮራ አገዳ ለማልማት የመስኖ ዝርጋታ
ለማከናወን የሚያስችል ጨረታ አውጥቶ ጨረታው በሂደት
ላይ የሚገኝ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡
በተያያዘም ለልማቱ ከሚፈለገው መሬት ላይ ተነሺ ለሆኑ
ዜጎች የማሕበራዊ ተቋማት ግንባታ ለማስፈጸም ከአካባቢው
አስተዳደር አካላት ጋር በመሆን እንቅስቃሴ እየተደረገ
እንደሚገኝ ዋና ስራ አስኪያጁ አመልክተዋል፡፡
»» ገጽ.12

9
የስኳር
ኮርፖሬሽን
በሚኒስትሮች
ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 192/2003
ከተቋቋመ ጀምሮ ላለፉት ሦስት
አመታት ኮርፖሬሽኑን በሚኒስትር
ማዕረግ በዋና ዳይሬክተርነት የመሩት
የአቶ አባይ ጸሐዬ ሽኝትና ከጥቅምት
2006 ዓ.ም ጀምሮ በሚኒስትር
ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና
ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት የአቶ
ሽፈራው ጃርሶ አቀባበል ሥነ ስርአት
11
ጣፋጭ ዜና መፅሄት

ስልጠና ተከታትለው የተመለሱ
ባለሙያዎች ልምዳቸውን አካፈሉ
ስልጠናውን ተከታትለው የተመለሱ ባለሙያዎቸ
በስኳር ኢንደስትሪ ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ
የሞሪሽየስ ተመራማሪዎችና ባለሙያዎች ያላቸውን
ዕውቀት፣ ልምድና ተሞክሮ ወደአገራችን መጥተው
የሚያካፍሉበት ሁኔታ ቢመቻች አገሪቱ ተጠቃሚ
ልትሆን እንደምትችልም ገልጸዋል ፡፡
ሰልጣኞቹ በስልጠናው ወቅት ላገኙት እውቀት፣
ልምድና ተሞክሮ እውቅና የሚሰጥ የምስክር
ወረቀት ከምርምርና ስልጠና ዘርፍ ምክትል
ዋና ዳይሬክተር ከአቶ ዮሐንስ መኳንንት እጅ
ተረክበዋል፡፡
በሌላ በኩል በሙከራ ማሳ ላይ የሚገኙትና
የምርምር ስራቸው ተጠናቆ ለተጠቃሚ ለማድረስ
የቴክኒክና የማኔጅመንት ክህሎት ያለው የዘር ማባዛት ስራ እየተሰራላቸው የሚገኙት N52
የሰው ሃይል ለማፍራት የሚያደርገውን ጥረት 219 እና N53 216 የተባሉት ዝርያዎች ተስፋ ሰጪ
ውጤት እያሳዩ እንደሚገኙ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ
ያግዛል፡፡
ጨምሮ አስታውቋል፡፡
ሰልጣኞቹ ለሌሎች ተመራማሪዎች
ከስልጠናው ያገኙትን ልምድ ባካፈሉበት ምርምሩን በመሪነት እያካሄዱ የሚገኙት አቶ
ወቅት ስልጠናውን በወሰዱበት አገር ምርምር አብይ ጌታነህ ዝርያዎቹ በአገዳ ብዛት፣ በስኳር
የሚሰራው በግለሰቦች ፍላጎት ሳይሆን ይዘታቸውና በሄክታር በሚሰጡት የምርት መጠን
የደንበኞችን ፍላጎት በመለየትና ችግሮችን በአሁኑ ወቅት በፋብሪካዎች ምርት ላይ ከሚገኘው
ለመፍታት ታስቦ በሚቀረጹ ፕሮጀክቶች B52 298 ከተባለው ጋር ሲነጻጸር የተሻሉ
መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ አክለውም ዝርያዎቹን
አማካይነት ነው ብለዋል፡፡
በሰፊው ወደ ተጠቃሚው ለማድረስ ዝግጅት
እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

ስልጠናው ትኩረት ካደረገባቸው መስኮች አንዱ የኬን ፋርም ማኔጅመንት ይገኝበታል

በሞሪሽየስ ለአንድ ወር በኬን ፋርም
ማኔጅመንት ፣ በኢሪጌሽን ፣ በሜካናይዜሽን፣
በኬሚካል ኮንትሮልና በሌሎች ጉዳዮች ላይ
ስልጠና ወስደው የተመለሱ የኮፖሬሽኑ
የምርምርና ስልጠና ዘርፍ ባለሙያዎች
ከስልጠናው ያገኙትን ልምድ ለተንዳሆ ስኳር
ፋብሪካ ባልደረቦች አካፈሉ፡፡
ፋብሪካው ለዜና መጽሔት ዝግጅት ክፍላችን
በላከው መረጃ እንዳመለከተው ስልጠናው
ኮርፖሬሽኑ የጀመራቸውን የስኳር ልማት
ስራዎች በላቀ ደረጃ ለማከናወን የሚያስችል

ፕሮጀክቱ አመታዊ እቅዱን ...
የበጀት አመቱን እቅድ ለማሳካት ቁልፍ ሚና ከሚኖራቸው
ዝግጅቶች መካከል አንዱ የሆነው የፕሮጀክቱን የሰው ሃይል
በአመለካካትና በክህሎት ማብቃት መሆኑን ዋና ስራ አስኪያጁ
ጠቁመው 139 የፕሮጀክቱ ስራ አመራሮችና ሠራተኞች በውጪ
አገር፣ በኮርፖሬሽኑና በፕሮጀክት ደረጃ በተለያዩ ርዕሶች
ስልጠና እንዲያገኙ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡
በፕሮጀክቱ በመካሄድ ላይ የሚገኘው ልማት ለአካባቢውና
ለአገሪቱ ምጣኔ ሐብት እድገት ሊኖረው በሚችለው ጠቀሜታ
12

ዙሪያ ለአካባቢው ህብረተሰብ ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ
መሆኑን ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸው ስራውን ከዞን፣ ከወረዳና
ከቀበሌ አመራሮች ለመጀመር አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶች
መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡
በተያያዘም ለልማቱ ከሚፈለገው መሬት ላይ ተነሺ ለሆኑ ዜጎች
የማህበራዊ ተቋማት ግንባታ ለማስፈጸም ከአካባቢው
የአስተዳደር አካላት ጋር በመሆን እንቅስቃሴ እየተደረገ
እንደሚገኝ ዋና ስራ አስኪያጁ አመልክተዋል፡፡
በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች
የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና ድጋፍ
ፈንድ አቋቋሙ
የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች
ኤች.አይ.ቪ
ቫይረስ
በደማቸው
የሚገኝባቸውን ሠራተኞችና ወላጆቻቸውን
በበሽታው ያጡ ህጻናትን በቋሚነት
ለመርዳት የሚያስችል የኤች አይ ቪ ኤድስ
መከላከልና ድጋፍ ፈንድ አቋቋሙ፡፡

በዚሁ ወቅት የስኳር ኮርፖሬሽን ኤች.አይ.ቪ
ኤድስ መከላከያ አስተባባሪ ወ/ሮ ካሰች
ሺበሺ በፋብሪካው ያለውን የኤች.አይ.ቪ
ኤድስ ስርጭትና የመከላከል ስራውን
በተመለከተ የዳሰሳ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡

ፋብሪካው ዕለቱን ምክንያት በማድረግ
የድጋፍ ፈንዱ የተቋቋመው የኤች.አይ.ቪ/ በሠራተኞች መዝናኛ ክበብ ባካሄደው ልዩ
ኤድስ ቀን ታህሳስ 5 ቀን 2006 ዓ.ም ዝግጅት በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ወላጆቻቸውን
በፋብሪካ ደረጃ በተከበረበት ወቅት ላጡ 46 ታዳጊ ህጻናት የ13 ሺ 8ዐዐ ብር
የድርጅቱ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ድጋፍ አድርጓል፡፡
ባደረጉት ውይይት ላይ በተደረሰ ስምምነት
ነው፡፡
በዝግጅቱ ላይ የፋብሪካው ከፍተኛ የሥራ
ኃላፊዎች ጨምሮ ሠራተኞች፣ የስኳር
በስምምነቱ መሰረት ሰራተኞቹ በየወሩ ኮርፖሬሽን ተወካዮችና የምሥራቅ ሸዋ ጤና
በቋሚነት ከወር ደመወዛቸው ብር 0.5 ቢሮ ተወካይ ተገኝተዋል፡፡
በመቶ ለመከላከልና ድጋፍ ስራው እንዲውል
ተስማምተዋል፡፡
በፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ቀደም ሲል
በሥነ ሥርዓቱ ላይ የወንጂ ሸዋ ስኳር የተቋቋመው የኤች. አይ.ቪ ኤድስ ፈንድ
ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አታክልቲ ለ20 በበሽታው ወላጆቻቸውን ላጡ ህጻናት
ተስፋይ የፋብሪካው ሰራተኞች በራሳቸው በየወሩ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ
ተነሳሽነት ቋሚ የኤች አይ ቪ ኤድስ ድጋፍና ይታወቃል፡፡ የፈንዱ የገቢ ምንጭ
መከላከል ፈንድ ለማቋቋም በመቻላቸው የሰራተኛው መዋጮና ከፋብሪካው በየአመቱ
ልባዊ ምሥጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የሚመደብ ገንዘብ መሆኑ ይታወሳል፡፡

የፋብሪካው ሰራተኞች ፈንዱን ለማቋቋም ቁርጠኝነታቸውን አሳይተዋል

13
ጣፋጭ ዜና መፅሄት

የፋብሪካው ሴት ሰራተኞች
በለውጥ ንቅናቄ ግንባር ቀደም
ሚና እንጫወታለን አሉ
ዘመቻው ላይ በመሳተፍ የሰራተኞቹን
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሴት ሠራተኞች በፋብሪካው
ዓላማ አበረታተዋል፡፡
በተጀመረው አጠቃላይ የለውጥ ንቅናቄ ግንባር ቀደም
ሚና እንደሚጫወቱ አስታወቁ፡፡
በጽዳት ዘመቻው ማጠቃለያ ሥነስርዓት ላይ ሁለቱም የሥራ ኃላፊዎች
‹‹በሴቶች የነቃ ተሳትፎ ምርታማነታችንን እናሳድጋለን››
ባስተላለፉት መልዕክት ከዚህ ቀደም
በሚል መሪ ቃል 220 የሚሆኑ የፋብሪካው ሴት
የነበረውን
የተዛባ
የሥርዓተ-ፆታ
ሠራተኞች ህዳር 1/2ዐዐ6 ዓ.ም በፋብሪካው የምርት ቦታ
አመለካከት በመለወጥ ሴቶችንና ወንዶችን
በመገኘት የጽዳት ዘመቻ ያካሄዱ ሲሆን፣ ያከናወኑት
በሁሉም ዘርፍ እኩል ተሣታፊና ተጠቃሚ
ተግባር በገንዘብ ሲተመን ከ 8 ሺህ ብር በላይ መሆኑ
ለማድረግ የተጀመረው ጥረት በአጭር ጊዜ
ታውቋል፡፡
ውጤታማ እየሆነ መጥቷል ብለዋል፡፡
የስኳር ኮርፖሬሽን ሥርዓተ-ፆታ ዳይሬክተር ወ/ሮ
ሴቶች አካባቢንና ማህበረሰብን ወደ
እንጉዳይ አሰፋ እንዲሁም የኮርፖሬሽኑ የኤች.አይ.ቪ./
መልካምና ወደ ምርታማነት የመለወጥ
ኤድስ መከላከያ አስተባባሪ ወ/ሮ ካሰች ሺበሺ በጽዳት
አቅም ያላቸው መሆኑን በመገንዘብ
የሴት ሰራተኞቹ የጽዳት ዘመቻ ከ 8 ሺ ብር
የፋብሪካው ሴት ሰራተኞች የጀመሩትን
በላይ የሚገመት ገንዘብ አድኗል
አርዓያነት ያለው ጥረት አጠናክረው
እንዲቀጥሉም አሳስበዋል፡፡
የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ
ዘነበ ይማም በወቅቱ ባደረጉት ንግግር
የፋብሪካውን ምርታማነት ለማሳደግ
እየተካሄደ ባለው አጠቃላይ የለውጥ
ንቅናቄ ውስጥ ሴት ሠራተኞች
የጀመሩትን ብርቱ ጥረት አጠናክረው
እንደሚቀጥሉና ፋብሪካውም በዚህ
አመት 1.3 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር
ለማምረት የያዘው ዕቅድ እንደሚሳካ
ያላቸውን ሙሉ እምነት ገልጸዋል፡፡
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የሥርዓተ
ፆታ ቡድን መሪ ወ/ሮ ዓለሚቱ ጉልቴ
በበኩላቸው የጽዳት መርሃ ግብሩ ዋና
አላማ ሴት ሰራተኞች ለፋብሪካው
ምርታማነትና እድገት ሊያከናውኗቸው
ከሚችሉት በርካታ ተግባራት ውስጥ
የፋብሪካውን የምርት ቦታ ጽዱ
በማድረግ ለስራ አመቺና ማራኪ
የሚሆንበትን ሁኔታ መፍጠር ነው
ብለዋል፡፡
14
በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

የስኳር ልማት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች
የሚገኙ ነዋሪዎች የልማቱ ተዋናዮች እየሆኑ ነው
የስኳር ልማት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች
የሚገኙ ነዋሪዎች የስኳር ልማቱን እንደሚፈልጉ
ከመግለፅ ባለፈ የልማቱ ተዋናዮች እየሆኑ
እንደሚገኙ ተገለጸ፡፡
የስኳር ኮርፖሬሽን የሕዝብ አደረጃጀት ዘርፍ
ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳመነ ዳሮታ ከዜና
መጽሔቱ ዝግጅት ክፍል ጋር ባደረጉት ቆይታ
የስኳር ልማት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች
የሚገኙ ነዋሪዎች ልማቱን እንደሚፈልጉት
ከመግለጽ ባለፈ ቀዳሚ ተዋናዮች እየሆኑ
ይገኛሉ ብለዋል፡፡
መንግስት ከፍተኛ ወጪ በማውጣት
እያከናወነ የሚገኘው የስኳር ልማት ልማቱ

የሚካሄድበትን አካባቢ ህብረተሰብ ይሁንታ
ካላገኘ ዋጋ እንደማይኖረው ይገነዘባል
ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በዚህ ረገድ
በልማቱ አጠቃላይ ሂደት ላይ በመወያየትና
በመተማመን እየሠሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

በዋናነት ልማቱ የሚከናወንበት አካባቢ
ሕብረተሰብ ከልማቱ ተጠቃሚ የሚሆንበትን
ስልት በመንደፍ ነው ያሉት አቶ ዳመነ ይህም
እስካሁን በተከናወኑ ሥራዎች በተግባር
መረጋገጡን አብራርተዋል፡፡

ሕብረተሰቡ የስኳር ልማቱ የራሱ መሆኑን
በመገንዘቡና በማመኑ በአንዳንድ ቦታዎች
“በነጻ የሸንኮራ አገዳ ለምን አንተክልም?”
በማለት ከመጠየቅ ባለፈ በበለስ የስኳር
ልማት ፕጀክት የሸንኮራ አገዳ በመትከል
የልማቱ አጋር መሆኑን በተግባር እያሳየ ይገኛል
ብለዋል፡፡
መንግስት የስኳር ልማቱን የእድገትና
ትራንስፎርሜሽን እቅድ አካል ሲያደርግ

የስራ እድል ፈጠራን በተመለከተ ለቀረበላቸው
ጥያቄ በሰጡት ምላሽ በ2005 ዓ.ም በነባር
ስኳር ፋብሪካዎችና በፕሮጀክቶች ለ60 ሺህ
ዜጎች የስራ እድል እንደተፈጠራላቸው ገልፀው
ይህ ጥረት ወደፊትም ተጠናክሮ ይቀጥላል
ብለዋል፡፡
ከአቶ ዳመነ ዳሮታ ጋር የተደረገው ሙሉ ቃለ
ምልልስ በገጽ 16 ተስተናግዷል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች የብሔር ብሐረሰቦችና ሕዝቦች ቀን...
የተዛቡ ግኝኙነቶችን በማረም የሕገ መንግስታዊ ስርአቱ አደጋ
የሆኑትን የሃይማኖት አክራሪነትንና ኪራይ ሰብሳቢነት መታገል
እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
አያይዘውም በስኳር ልማት ዘርፍ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን
እቅድ የተቀመጡትን ግቦች እውን ለማድረግ የዋናው መስሪያ
ቤት፣ የፋብሪካዎችና የፕሮጀክቶች ሠራተኞች በህብረት በመስራት
የሕገ መንግስቱን ዓላማዎች ማሳካት እንደሚጠበቅባቸው
አመልክተዋል፡፡
ሕገ መንግስቱ የፀደቀበትን ቀን ማክበር ሠራተኞች እርስ
በርሳቸው እንዲተዋወቁ ያስችላል ያሉት አማካሪው ሕገ
መንግስቱን ተከትለው ከወጡ የልማት እቅዶች መካከል አንዱ
የሆነውን የስኳር ልማት ዘርፍ ስኬትን ለማረጋገጥ የኮርፖሬሽኑ
አመራርና ሰራተኛ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ጥረት ማድረግ
እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋል፡፡

በቀጣይም አንድ ጠንካራ የፖለቲካና የምጣኔ ሐብት ማሕበረሰብ
ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች
የዘርፉን እቅዶች ለማሳካት በትጋት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በእለቱ «የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
መንግስትና ሕብረ ብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓት « በሚል ርእስ
የመነሻ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ሕገ መንግስቱን
የተመለከቱ የጥያቄና መልስ ውድድሮችም ተካሂደዋል፡፡
ይህ የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በስኳር ፋብሪካዎችና
በፕሮጄክቶችም በድምቀት ተከብሯል፡፡
በተያያዘም የዓለም ኤድስ ቀንና የነጭ ሪቫን ቀን በዕለቱ
በኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ታስቦ ውሏል፡፡

የበዓሉ ታዳሚዎች

15
ጣፋጭ ዜና መፅሄት

በኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየሦስት ወሩ እየታተመ የሚወጣው ጣፋጭ
ዜና መጽሔት በዚህ ወር ዕትሙ የስኳር ልማት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች
የሚኖረው ህዝብ የልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆን እየተከናወኑ ስላሉ ሥራዎች
እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ከስኳር ኮርፖሬሽን የሕዝብ አደረጃጀት ዘርፍ
ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳመነ ዳሮታ ጋር ያደረገው ቆይታ እንደሚከተለው
ቀርቧል ፡፡

ጣፋጭ- በያዝነው በጀት ዓመት በመንደፍ ነው፡፡ በመሆኑም እስከ አሁን የጤና ተቋማት፣ የአርሶ አደር ማሰልጠኛ
የዘርፉ ዋነኛ የሥራ ትኩረት ምን በበለስ ስኳር ልማት አካባቢ በአማራ ክልል ማዕከላት፣ የቀበሌ ጽ/ቤቶች፣ የፖሊስ
በጃዊ ወረዳ በሁለት ሠፈራ ጣቢያዎች ጣቢያዎች፣ የውሃ ተቋማት፣ መዳረሻ
እንደሆነ ቢገልጹልን?
(አሊኩራንድና ኩምብር)፣ በቤኒሻንጉል መንገዶች እና መሰል ማህበራዊ ተቋማት
አቶ ዳመነ - ኮርፖሬሽኑ የስኳር ምርት ጉሙዝ ክልል በፓዌና ዳንጉር ወረዳዎች እየተገነቡና የተጠናቀቁት አገልግሎት
ከውጪ ማስገባትን በማስቀረት የአገር በሁለት ሠፈራ ጣቢያዎች (አባወሬኛና እየሰጡ ይገኛሉ፡፡
ውስጥ ፍጆታን ከማሟላት ባሻገር ወደ ባንባጅዋ) እና በወልቃይት በቆራሪት ሠፈራ
እንዲሁም በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት
ውጪ አገር ኤክስፖርት ለማድረግ ጣቢያ መልሰው ለሚቋቋሙ የህብረተሰብ
ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ያለውን ጥረት ክፍሎች አገልግሎት የሚሰጡ ት/ቤቶች፣ አካባቢ በቦዲ ሦስት መንደሮች፣ በጉራ
ውጤታማ ለማድረግ የኢንዱስትሪ
አካባቢ ሠላም መሆን ወሳኝ ነው፡፡
ስለሆነም የዘርፉ የበጀት ዓመቱ የትኩረት
አቶ ዳመነ ዳሮታ
በስኳር ኮርፖሬሽን የሕዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር
አቅጣጫ የኮርፖሬሽኑ የልማት ዕቅድ
ተፈፃሚ እንዲሆን የበኩሉን ድርሻ
መወጣትና በሂደትም በልማት አካባቢው
የሚገኝ ህብረተሰብ ከልማቱ ተጨባጭ
ተጠቃሚነቱን እያረጋገጠ እንዲሄድ
ከክልል መንግስታት ጋር በቅንጅት
መሥራት ነው፡፡
ጣፋጭበስኳር
ፋብሪካዎችና
ኘሮጀክቶች
አካባቢ የሚገኘው
ህብረተሰብ
የልማቱ
ዋንኛ
ተጠቃሚ
እንዲሆን እስካሁን
የተከናወኑ ሥራዎችን (ከማህበራዊ
አገልግሎቶችና ከመሰረተ ልማት
ግንባታ፣ ከሥራ ዕድል ፈጠራ፣
ከሥልጠና ….. አኳያ ) ጠቅለል
አድርገው ቢያብራሩልን?
አቶ ዳመነ - መንግስት የስኳር ልማትን
የእድገትና
ትራንስፎርሜሽን
እቅድ
አካል ሲያደርግ በዋነኝነት ልማቱ
የሚከናወንበት አካባቢ ህብረተሰብ
ከልማቱ ተጠቃሚ የሚሆንበትን ስልት
16
በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

አንድ መንደርና በሃይለ ውሃ ሁለት
መንደሮች በአጠቃላይ በስድስት መንደሮች
በእያንዳንዳቸው ከአስር በላይ ማህበራዊ
ተቋማትና የመሠረተ ልማት አውታሮች
እየተገነቡ ያለበት ሁኔታ ሲኖር የቦዲ ሦስት
መንደሮች ተጠናቀው ለአርብቶ አደሮች
አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ከዚህም
ሌላ በኮርፖሬሽኑ እና በደቡብ ብ/ብ/ እና
ሕዝቦች ክልል የጋራ በጀት በማኪ ወንዝ
አካባቢ በአንድ መንደርና በሻርማ ወንዝ
አካባቢ በሁለት መንደሮች አርብቶ አደሮች
ቀደም ሲል በሚኖሩበት አካባቢ የውሃ
አማራጭ በመገኘቱ ባሉበት አገልግሎት
እንዲያገኙ
የማህበራዊ
ተቋማትና
የመሠረተ ልማት አውታሮች እየተገነቡ
ናቸው፡፡

(TVET) ጋር በመቀናጀት በኮርፖሬሽኑ
ሙሉ ወጪ የመለስተኛ ሙያ ስልጠና
እንዲያገኙ እየተደረገ ይገኛል፡፡ በዚህ
መሰረት በኩራዝ 232፣ በበለስ 79 እና
በወልቃይት 204 ወጣቶች በተለያዩ
የኮንስትራክሽን ሙያዎችና በትራክተር
ኦፕሬተርነት
ስልጠና
አግኝተው
በፕሮጀክቶቹ እንዲቀጠሩ ተደርጓል፡፡ ይህ
ወደፊትም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

ጣፋጭ- ከካሳ ክፍያ፣ ከመልሶ
ማቋቋም
(መንደር
ማሰባሰብ፣
ሰፈራ) እና በመስኖ ከሚለማ መሬት
ርክክብ ሥራዎች
ጋር በተያያዘ
የተከናወኑ ተግባራትን ቢገልጹልን?
በዚህ ረገድ አልፎ አልፎ ከህብረተሰቡ
የሚቀርቡ ቅሬታዎች በምን አግባብ
በፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ይዞታ ውስጥ እየተፈቱ ነው?
ህጋዊ መሠረት ሳይኖራቸው ለረጅም ጊዜ
የቆዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ከፋብሪካው አቶ ዳመነ -የሀብት ቆጠራና ካሳ ክፍያም
አስተዳደር ወሰን ውጪ ለማስፈር በአዲሱ ሆነ ዜጎችን መልሶ ማቋቋም ስራዎችን
የሰፈራ ጣቢያ ከስምንት በላይ ማህበራዊ የምናከናውነው
ልማቱ
ከሚገኝበት
ተቋማት እየተገነቡ ሲሆን፤
በአርጆ ክልል ጋር
በመቀናጀት ነው፡፡
ዲዴሳ፣ በወንጂ ሸዋ እና በመተሐራ ስኳር በመሆኑም እስከ አሁን ባለው ሂደት የጎላ
ፋብሪካዎች አካባቢ ለሚገኙ የህብረተሰብ ችግር አላጋጠመንም ብሎ መውሰድ
ክፍሎች አገልግሎት የሚሰጡ ማህበራዊ ይቻላል፡፡ በበለስና በወልቃይት ስኳር
ተቋማትን ለመገንባት እየተንቀሳቀስን ልማቶች ምክንያት መልሰው የሚሰፍሩ
እንገኛለን፡፡
ዜጎች በአዋጁ መሠረት ሀብትና ንብረት
ተገምቶ ካሳ እንዲከፈላቸው እየተደረገ
በሌላም በኩል በውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ነው፡፡
ሚኒስቴር ባለቤትነት በተንዳሆ ስኳር
ፋብሪካ አካባቢ ለሚገኙ አርብቶ አደሮች በኩራዝ አካባቢ የሚገኘው መሬት ቀደም
በዱብቲ ወረዳ በአስር መንደሮች ሲል በአርብቶ አደሮች ተይዞ በቋሚነት
በእያንዳንዳቸው
የሰባት
ማህበራዊ የለማ ንብረትና ሀብት የሌለ በመሆኑ
ተቋማት ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን፣ እስከ አሁን ድረስ የካሳ ክፍያ ያልተፈፀመ
ተቋማቱ በከፊል አገልግሎት እየሰጡ ቢሆንም የአርብቶ አደሩን ኑሮ በዘላቂነት
ይገኛሉ፡፡ በከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክት ለመለወጥ መንግስት ከፍተኛ ወጪ
አካባቢም ለሚገኙ አርብቶ አደሮች በማውጣት የመስኖ መሰረተ ልማት
ተመሳሳይ አገልግሎት እንዲያገኙ እየተሰራ በመስራት አርብቶ አደሩ ተጠቃሚ
ነው፡፡
እንዲሆን እየሰራ ይገኛል፡፡ በተንዳሆና
በከሰምም በመንግስት ከፍተኛ ወጪ
ከስራ ዕድል ፈጠራ አንፃር በነባር የመስኖ መሰረተ ልማት ለአካባቢው
ስኳር
ፋብሪካዎችና
ፕሮጀክቶች አርብቶ አደሮች እየተገነባ ይገኛል፡፡
በ2005 ዓ.ም ወደ 60 ሺህ የስራ ዕድል
ተፈጥሯል፡፡ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ጣፋጭየስኳር
ልማት
ዘመን መጨረሻ በዘርፉ ከ200 ሺህ በላይ በሚካሄድባቸው
አካባቢዎች
ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ይፈጠራል፡፡
የህዝብ ንቅናቄ በመፍጠር ህዝቡ
በተለይ በልማቱ አካባቢ የሚኖሩ ዜጎች በባለቤትነት ስሜት ተነሳስቶ የልማቱ
በሚፈጠሩ የስራ ዕድሎች ይበልጥ አጋዥ ኃይል እንዲሆን እየተከናወኑ
ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ከቴክኒክና የሚገኙ ሥራዎችን
ቢያብራሩልን
ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ፡፡ ምንስ ውጤት ተገኝቷል?

አቶ ዳመነ - ምንም እንኳ መንግስት
ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ለአገርና ልማቱ
ለሚከናወንበት አካባቢ የጎላ ጠቀሜታ
ያለው ልማት እያከናወነ ቢሆንም
ህብረተሰቡ ሳያምንበት በጫና የሚፈፀም
ልማት ዋጋ የማይኖረው መሆኑን ከማንም
ይልቅ ይገነዘባል፡፡ በመሆኑም ወደ
የትኛውም ስራ ከመግባታችን በፊት
ስለልማቱ አጠቃላይ ሂደት ከህብረተሰቡ
ጋር በመወያየትና በመተማመን እየሄድን
እንገኛለን፡፡
ውጤቱንም ስንመለከት በልማቱ አካባቢ
ያሉ ነዋሪዎች ልማቱን እንደሚፈልጉ
ከመግለፅ ባለፈ የልማቱ ቀዳሚ ተዋናዮች
እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ በአንዳንድ ቦታዎችም
የሸንኮራ አገዳ ተከላ ሳይቀር “ በነፃ ለምን
አንተክልም” ከማለት ባለፈ በበለስ የስኳር
ልማት ፕሮጀክት የሸንኮራ አገዳ በመትከል
አጋርነታቸውን
እየገለጹ
ናቸው፡፡
በአጠቃላይ የገባኸውን ቃል ወደ ተግባር
መለወጥ እስከ ቻልክ ድረስ ህብረተሰቡ
ከልማት ፍላጎት ባለፈ የባለቤትነት ስሜት
እያደረበት ይሄዳል፤ አሁንም እየታየ ያለው
ይህ ነው፡፡
ጣፋጭ- የሸንኮራ አገዳ አብቃዮችን
እና አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማትን
በማደራጀት፣
በማስተባበርና
በመከታተል ረገድ ምን ያህል
ርቀት
ተጉዛችኋል?
የሥራችሁን
መገለጫዎች ቢጠቅሱልን?
አቶ ዳመነ - እንደሚታወቀው የሸንኮራ
አብቃይ አርሶ አደሮች የህብረት ስራ
ማህበራት ልምድ ያለው በወንጂ ሸዋ
ስኳር ፋብሪካ ነው፡፡ የማደራጀት ስራው
የሚሰራው ከማህበራት ማደራጃ ጽ/ቤቶች
ጋር በመቀናጀት ሲሆን አርሶ አደሩ ከመሬት
ይዞታው ሳይፈናቀል የልማቱ ቀኝ እጅ
በመሆን ሸንኮራ እያመረተ ለፋብሪካው
እንዲያቀርብ እና ተጠቃሚ እንዲሆን
እየተደረገ ይገኛል፡፡
በዚህ ሂደት እስከ አሁን 31 መሠረታዊ
የህብረት ስራ ማህበራት እና አንድ ዩኒየን
የተቋቋሙ ሲሆን በልማቱ ዙሪያ ያሉ
ችግሮችና የመፍትሄ አቅጣጫን በተመለከተ
ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት
ጋር በመሆን ዝርዝር ጥናት በማጥናትና
ከአርሶ አደሩ ጋር በመተማመን በየጊዜው
»» ገጽ.18

17
ጣፋጭ ዜና መፅሄት

እኛ የምንሰራው ለህዝብ ነው፤
ህዝቡ ያላመነበትና ተጠቃሚ
የማይሆንበትን ልማት
አንሰራም ”
የሚያጋጥሙትን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል
ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ስራ ገብተናል፡፡

መለወጥ የማይፈልጉ አካላት የሐሰት ውንጀላ
ነው፡፡

በሌላ በኩል በተለይ በአዳዲስ ፕሮጀክቶች
አካባቢ የጥቃቅንና አነስተኛ አንቀሳቃሾች የስራ
ዕድል እንዲፈጠርላቸው ከሚመለከታቸው
የመስተዳድር አካላት ጋር እየሰራን በመሆኑ ብዙ
ወጣቶችና ሴቶች ተጠቃሚ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡

ይልቁንም አርብቶ አደሩ በልማት ክልሉ
ውስጥ የአኗኗር ባህሉና ወጉ ሳይዛባ በመንደር
እየተሰባሰበ ውሃን ማዕከል ያደረገ የመስኖ
መሠረተ ልማት የሚሰጠውና የማህበራዊ
ተቋማት የሚገነቡለት በመሆኑ ሌሎች ይህንን
ለውጥ እያዩ ለምን ፈጥናችሁ ወደ እኛም
አትመጡም እያሉን ነው ፡፡

ጣፋጭ - ልማቱን ከማፋጠን አንጻር
ከክልሎች ፣ ከዞኖች ከወረዳዎችና
ከሌሎች የባለ ድርሻ አካላት ጋር ያላችሁ
ግንንኙነት ምን ይመስላል?
አቶ ዳመነ - የእኛ ስራ ከህዝብ ጋር በቀጥታ
የተገናኘ
እንደመሆኑ
መጠን
ልማቱ
ከሚገኝባቸው ክልሎች ጋር በቅርበት የምንሰራ
ሲሆን ክልሎች የስኳር ልማት ስቲሪንግ
ኮሚቴ በማዋቀር ለስራው ትኩረት በመስጠት
በባለቤትነት እየመሩት ይገኛሉ፡፡ እስከ አሁን
ያለን ግንኙነት መልካም የሚባል ነው፡፡

እንዲሁም በአርሶ አደር አካባቢዎች ተገቢው
ካሳ የሚከፈልና መሟላት ያለበት ማህበራዊ
ተቋምና የመሠረተ ልማት አውታሮች ከነበረው
ተመጣጣኝና በተሻለ ሁኔታ እየተገነባ
ነው፡፡ የተለያዩ የስራ ዕድሎች እየተፈጠሩ
በመሆናቸው ተነሺው ህብረተሰብ በተጨባጭ
ተጠቃሚ መሆኑን ስለተገነዘበ የልማቱ አጋር
እየሆነ ይገኛል፡፡

በሌላ በኩል የሸንኮራ አገዳ ልማት የአረንጓዴ
ልማት አካል እንደመሆኑ መጠን የአካባቢ
ጣፋጭ- «በስኳር ልማት ሳቢያ ህዝብ አየር ንብረት በመጠበቅ
አዎንታዊ የሆነ
ተፈናቀለ፣ ሰብዓዊ መብቱ ተጣሰ፣ ሚናን ይጫወታል፡፡ ከእምነት ቦታ አንፃርም
ለዜጎች ተገቢው ካሳ አልተከፈለም፣ በአንዳንድ የውጪ ሚዲያ ሳይቀር ብዙ ሲባል
ደን ተመነጠረ፣ ቅርሶች አልተጠበቁም፣ የነበረው የዋልድባ ገዳም ተደፈረ የሚል
የእምነት
ቦታ
ተደፈረ.»
የሚሉ ነበር፡፡ ልማቱ በገዳሙ ላይ የሚያመጣው
ተደጋጋሚ ስሞታዎች
(በተለይም ተፅዕኖ የሌለ ቢሆንም አንዳንድ የተለየ ፍላጎት
ደግሞ የኩራዝ ስኳር ልማት ኘሮጀክት ያላቸው አካላት አጀንዳ ለማድረግ በሰፊው
በሚካሄድበት
አካባቢ)
የሰብዓዊ ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ሆኖም በአካባቢው ያለው
መብትና የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋች ነን ህብረተሰብ ሁኔታውን በቅርበት የሚያውቀውና
በሚሉ ተቋማትና በአንዳንድ የውጭ የሚገነዘበው በመሆኑ ለልማቱ ያለውን አጋርነት
ሚዲያዎች
ይናፈሳሉ፡፡ በዚህ ላይ እየገለፀ ይገኛል፡፡
የእርስዎ ምላሽ ምንድ ነው?
በአሁኑ ጊዜ በተሳሳተ አቅጣጫ ሲጓዙ የነበሩ
አቶ ዳመነ - በየጊዜው በተለያዩ ፍትሐዊነት ጭምር ስህተት መሆኑን በማመን ከመንግሥትና
በጎደላቸው ተቋማት የሚናፈሱ አሉባልታዎችና ከሕዝብ ጎን በመቆም ልማቱን ለመደገፍ ጥያቄ
ተጨባጭ
እውነታውን
ስንመለከተው እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ በአጠቃላይ በሁሉም
የማይገናኝበት
ሁኔታ
ነው
ያለው፡ አካባቢ ያለው ህዝባችን የልማቱን ፋይዳ
፡ እኛ የምንሰራው ለህዝብ ነው፤ ህዝቡ በመገንዘብ የራሱን አስተዋፅዖ እያበረከተ የሚገኝ
ያላመነበትና ተጠቃሚ የማይሆንበትን ልማት በመሆኑ የሰብዓዊ መብትና የአካባቢ ጥበቃ
አንሰራም፡፡ በደቡብ ኦሞ መንግስት ህዝቡን ተሟጋች ነን የሚሉ አካላት ይህንኑ በማመን
በኃይል እያፈናቀለ መሆኑን የሚናገሩ
አሉ ከአፍራሽ ቅስቀሳቸው ቢቆጠቡ መልካም ነው
፡፡ ይህ ከእውነት የራቀ እና የአርብቶ አደሩን እላለሁ፡፡
18
ጣና በለስ

እናስተዋውቃችሁ

የተቀናጀ የስኳር ልማት ፕሮጀክት
ከአምስት አመታት በፊት በ2001
ዓ.ም ነበር በአማራ ብሔራዊ ክልል
«ጣና የተቀናጀ የመስኖ ልማት
ፕሮጀክት» የተጀመረው፡፡ የእድገትና
ትራንስፎርሜሽን እቅድ በተጠነሰሰበት
በ2003 ዓ.ም የአካባቢውን እምቅ
አቅም እንዲሁም አዋጭነቱን ከግምት
ውስጥ
በማስገባት
የሚኒስትሮች
ምክር ቤት በደንብ ቁጥር 192/2003
ፕሮጀክቱ «ጣና በለስ የተቀናጀ ስኳር
ልማት ፕሮጀክት» በሚል ስያሜ
በስኳር ኮርፖሬሽን ስር እንዲሆን
አደረገው፡፡ ከዚህ ጊዜ አንስቶ
ፕሮጀክቱን እውን ለማድረግ የተለያዩ
ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ነው፡
፡ የወንዙን አቅጣጫ በማስቀየር
የተሰራውና 13 ሜትር ቁመትና
በሰከንድ 60 ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ
የመልቀቅ አቅም ያላቸው ስድስት
በሮችን ያካተተው
ዘመናዊ የውሃ
መቀልበሻ አናት (ዊር) የሰሜን ጎንደሩ
አለፋ ወረዳ ፣ የምዕራብ ጎጃሙ ደቡብ
አቸነፈርና የአዊ ዞኑ ጃዊ ወረዳዎች
በሚዋሰኑበት ስፍራ ላይ ይገኛል፡፡
ውሃው ወደ እርሻ ማሳዎች እንዲደርስ
ለማድረግም 31 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው
ዋና ካናል ተገንብቷል፡፡

በፕሮጀክቱ የእስከአሁን እንቅስቃሴ
ከ17,ዐዐዐ ሄክታር በላይ መሬት ከሦስተኛ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ወገን ነፃ በማድረግ ለአገዳ እርሻ ዝግጁ
በአዊ ዞን በጃዊ ወረዳ እንዲሁም ከመደረጉም በላይ ውሃ ወደ አገዳ እርሻ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ ለማሰራጨት ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡
መንግሥት በመተከል ዞን በፖዊና ዳንጉር እስከ ህዳር 2006 ዓ.ም አጋማሽ ድረስ
ወረዳዎች ውስጥ የሚገኘው የጣና በለስ 2,724 ሔክታር መሬት ሙሉ በሙሉ
የተቀናጀ የስኳር ልማት ፕሮጀክት በሸንኮራ አገዳ ዘር በመሸፈን ለሚገነቡ
የጃዊ ፣ ፓዊና ዳንጉር ሜዳዎችን ፋብሪካዎች የሙከራ ተግባርና የዘር
ተንተርሶ የሚፈሰውን የበለስ ወንዝን አቅርቦት በራሱ በፕሮጀክቱ እየተሸፈነ
አቅጣጫ በማስቀየር 75 ሺ ሄክታር ይገኛል፡፡
መሬት (50ሺህ ሄክታር በአማራ ክልል
እንዲሁም 25ሺህ ሄክታር በቤኒሻንጉል የበለስ የተቀናጀ የስኳር ልማት
ክልል) ላይ የሸንኮራ አገዳና ሌሎች ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ እያንዳንቸው በቀን
ተፈላጊ ሰብሎችን እንዲያመርት ታስቦ 12 ሺ ቶን የሸንኮራ አገዳ የመፍጨት
የተጀመረ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው፡፡
አቅም ያላቸው ሦስት ፋብሪካዎች /
በለስ ቁጥር 1፣ በለስ ቁጥር 2 እና አይማ
ፕሮጀክቱ ከአዲስ አበባ በዳንግላ ፋብሪካ/ ይኖሩታል፡፡ በ75 ሺህ ሄክታር
መስመር 558 ኪ.ሜ ወይም በሌላኛው መሬት ላይ የሚለማን ሸንኮራ አገዳ
አማራጭ መንገድ
ከአዲስ አበባ በግብአትነት የሚጠቀሙት እነዚህ
በኮሶበር ቻግኒ 597 ኪ.ሜ ላይ ይገኛል፡ ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው ማምረት
፡ የፕሮጀክቱ ዋና ጽ/ቤት «መለስ ዜናዊ ሲጀምሩ በድምሩ በዓመት 726ሺህ ቶን
ጠቅላይ ሰፈር» ከጃዊ ወረዳ ዋና ከተማ ወይም 7 ሚሊዮን 260 ሺህ ኩንታል
ፈንደቃ በአንድ ኪ.ሜ ርቀት ላይ ስኳር የማምረት አቅም ይኖራቸዋል።
በሚገኝ ቆላማ የአየር ንብረት ባለው ከዚህ በተጨማሪ ከስኳር ተረፈ ምርት
አካባቢ የከተመ ነው፡፡
በአመት 62.4 ሚሊዮን ሊትር ኢታኖል
እና 165 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል
ፕሮጀክቱ ለመስኖ ስራ የሚጠቀምበትን እንደሚያመርቱም ይጠበቃል፡፡ ይህም
የበለስ ወንዝን አቅጣጫ የማስቀየር አገራችን ተግባራዊ በማድረግ ከዓለም
ስራ ሙሉ ለሙሉ የተከናወነው ግንባር ቀደም የሆነችበትን የአረንጓዴ

ልማት ስትራቴጂን በመደገፍ ረገድ
ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ዓላማዬ ብሎ ከያዛቸው ዋና
ዋና ተግባራት አንዱ ለዜጐች የሥራ
እድል ፈጠራን ማመቻቸት ነው፡
፡ በዚህም መሠረት በአሁኑ ጊዜ ለ1ዐ
ሺ 6ዐ3 ወንዶችና ለ3ሺ742 ሴቶች
በአጠቃላይ ለ14ሺ345 የአካባቢው
ነዋሪዎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ እድል
ፈጥሮላቸዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅም
ከ69 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚና
ጊዜያዊ የስራ እድል እንደሚፈጥር
ይጠበቃል፡፡
በ2ዐዐ4 ዓ.ም ፕሮጀክቱ በሚገነባበት
አካባቢ ይኖሩ ለነበሩና እንዲሰፍሩ
ለተደረጉ 1,909 የጃዊ ወረዳ የቤተሰብ
ኃላፊዎች የመኖሪያና የእርሻ ቦታ
ከመመቻቸቱም ባሻገር 53 ሚሊዮን
ብር የካሣ ክፍያ ተሰጥቶ በአግባቡ
በተመረጠላቸው ቦታ ሰፍረው የተረጋጋ
ኑሮ በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ነዋሪዎቹ
በሰፈሩባቸው አካባቢዎች ደረጃቸውን
የጠበቁ ትምህርት ቤቶች ፣ የሰውና
የእንስሳት ጤና ኬላዎች ፣ የንጹህ
መጠጥ ውሃ ተቋማት ፣ ክረምትና
በጋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል
መንገድ በከፍተኛ ወጪ ተገንብተው
የአገልግሎቶቹ ተጠቃሚ እንዲሆኑ
ተደርጓል፡፡
ለስኳር ልማቱ መፋጠን አስተዋጽኦ
ለማድረግ
በፈቃዳቸው
መኖሪያ
አካባቢያቸውን እና የእርሻ መሬታቸውን
ትተው ከተነሱ የአካባቢው ማሕበረሰብ
ልጆች ውስጥ 1ዐኛ ክፍልን አጠናቀው
ስራ አጥ የነበሩ 30 ወጣቶችን
በመመልመል በጫንጮ ትራክተር
ኦፕሬተር ማሰልጠኛ ለሦስት ወር
እንዲሰለጥኑ ተደርጎ በፕሮጀክቱ በቋሚ
ሠራተኛነት ተቀጥረዋል፡፡ በዚህም
ፕሮጀክቱ
ለህብረተሰቡ
ያለውን
አጋርነት በተግባር አስመስክሯል፡፡
19
ጣፋጭ ዜና መጽሔት
በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽኝ ዳይሬክቶሬት
በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት

www.etsugar.gov.et
:+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 A.A etsugar@hotmail.com

www.facebook.com/etsugar

More Related Content

Similar to ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 ታህሳስ 2006

ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ  2009 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ  2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ 2009 ዓ.ምEthiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007Ethiopian Sugar Corporation
 
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts - ታህሳስ 2006
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006 የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts - ታህሳስ 2006 Ethiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ምEthiopian Sugar Corporation
 
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያየስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያEthiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
 ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ምMeresa Feyera
 
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያየስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያEthiopian Sugar Corporation
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ምEthiopian Sugar Corporation
 
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ምየስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ምEthiopian Sugar Corporation
 
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽርየስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽርEthiopian Sugar Corporation
 

Similar to ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 ታህሳስ 2006 (14)

ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4 ቁጥር 4 ሰኔ 2008
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቅፅ 4. ቁጥር 1 መስከረም 2008
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ  2009 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ  2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 2-ታህሳስ 2009 ዓ.ም
 
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007
 
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts - ታህሳስ 2006
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006 የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts  - ታህሳስ 2006
የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃዎች || Sugar Corporation Facts - ታህሳስ 2006
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 4-ሰኔ 2009 ዓ.ም
 
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያየስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
 ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት ቅፅ 5 ቁጥር 3-መጋቢት 2009 ዓ.ም
 
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያየስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ
 
ጣፋጭ ዜና መፅሄት ቁጥር 3
ጣፋጭ ዜና መፅሄት ቁጥር 3ጣፋጭ ዜና መፅሄት ቁጥር 3
ጣፋጭ ዜና መፅሄት ቁጥር 3
 
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ምጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ም
ጣፋጭ ዜና መፅሔት - ልዩ እትም ታህሳስ 2011 ዓ.ም
 
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ምየስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም
 
#LIDI Ankelba 2011 magazen
#LIDI Ankelba 2011 magazen#LIDI Ankelba 2011 magazen
#LIDI Ankelba 2011 magazen
 
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽርየስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
የስኳር ኢንዱስትሪ እድገት ንጽጽር
 

More from Ethiopian Sugar Corporation

Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019Ethiopian Sugar Corporation
 
Investment opportunities in ethiopian sugar industry [ministry of finance]
Investment opportunities in ethiopian sugar industry  [ministry of finance]Investment opportunities in ethiopian sugar industry  [ministry of finance]
Investment opportunities in ethiopian sugar industry [ministry of finance]Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018 Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018 Ethiopian Sugar Corporation
 
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017Ethiopian Sugar Corporation
 
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2 December , 2016
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2  December , 2016Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2  December , 2016
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2 December , 2016Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December  2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.2 December  2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationEthiopian Sugar Corporation
 

More from Ethiopian Sugar Corporation (17)

Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
Sweet News Letter - Special Edition - September 2019
 
Ethiopian Sugar Industry Profile
Ethiopian Sugar Industry ProfileEthiopian Sugar Industry Profile
Ethiopian Sugar Industry Profile
 
Request for Information [RFI]
Request for Information [RFI] Request for Information [RFI]
Request for Information [RFI]
 
Investment opportunities in ethiopian sugar industry [ministry of finance]
Investment opportunities in ethiopian sugar industry  [ministry of finance]Investment opportunities in ethiopian sugar industry  [ministry of finance]
Investment opportunities in ethiopian sugar industry [ministry of finance]
 
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018 Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
Sweet Newsletter Special Edition, December, 2018
 
Ethiopian sugar industry profile
Ethiopian sugar industry profileEthiopian sugar industry profile
Ethiopian sugar industry profile
 
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 4 June , 2017
 
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2 December , 2016
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2  December , 2016Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2  December , 2016
Ethiopian Sugar Corporation Newsletter (Sweet ) - Vol. 5 No. 2 December , 2016
 
Ethiopian Sugar Industry Profile
Ethiopian Sugar Industry ProfileEthiopian Sugar Industry Profile
Ethiopian Sugar Industry Profile
 
Comparison of the sugar industry
Comparison of the sugar industryComparison of the sugar industry
Comparison of the sugar industry
 
External vacancy
External vacancyExternal vacancy
External vacancy
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.4 June 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.3 March 2016 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December  2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.2 December  2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.2 December 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.4. No.1 September 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.4 June 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
 
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar CorporationSweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
Sweet Newsletter Vol.3. No.3 March 2015 , by Ethiopian Sugar Corporation
 

ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 ታህሳስ 2006

  • 1. ጣፋጭ ዜና መፅሔት ራዕይ፡ በቀጣይ ዕድገት ላይ የተመሰረተና በአለም ተወዳዳሪ የሆነ የስኳር ኢንዱስትሪ መፍጠር ቅፅ 2. ቁጥር 2 -ታህሳስ 2006 www.etsugar.gov.et.com || www.facebook.com/etsugar ኮርፖሬሽኑ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን ከተቀመጠው የስኳር ልማት ንዑስ ዘርፍ ግብ 70 በመቶውን ማሣካት ይችላል • የእቅድ ዘመኑን የስኳርና ተጓዳኝ ምርቶች ግብ ተደራሽነት የሚያመለክት ፍኖተ ካርታ (Roadmap) ተዘጋጀ ስኳር ኮርፖሬሽን በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመኑ ከሚገነባቸው የስኳር ፋብሪካዎች ውስጥ ሰባቱን በእቅድ ዘመኑ መጨረሻ ድረስ ምርት በማስጀመር የዕቅዱን 70 በመቶ ማሣካት የሚያስችለው ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ መሰረት በዚህ ዓመት ተንዳሆ 1 እንዲሁም በ2007 ዓ.ም ተንዳሆ 2፣ ኩራዝ 1፣ ከሰም፣ በለስ 1 እና 2 እና አርጆ ዲዴሳ ተጠናቀው ምርት ይጀምራሉ፡፡ በሌላ በኩል ወልቃይት፣ በለስ 3 እና ኩራዝ 2 እና 3 በ2ኛው ምዕራፍ የዕቅድና ትራንስፎርሜሽን ዘመን የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ምርት ማምረት ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ »» ገጽ.3 የዓለም ኤድስ ቀን በአገር አቀፍ ደረጃ በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ተከበረ 25 ኛው ደረጃ በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ተከበረ፡፡ የዓለም ኤድስ ቀን “አንድም በበዓሉ ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፕሬዚዳንት ሰው በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እንዳይያዝ ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ፣ የጤና ጥበቃ ኃላፊነታችንን በመወጣት የአገራችንን ሕዳሴ ሚኒስትሩ ዶክተር ከሰተብርሀን አድማሱ ፣ እናሳካ!” በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ »» ገጽ.5 የሸንኮራ አገዳ አብቃይ ህብረት ሥራ ማህበራት ከወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ጋር ለጋራ ጥቅም ለመስራት ተስማሙ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ እና የሸንኮራ አገዳ አብቃይ አርሶ አደሮች ህብረት ሥራ ማህበራት የጋራ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከህዳር 7–14/2006ዓ.ም ውይይት አካሂደዋል፡፡ በመጀመሪያው ዙር ከህዳር 7-13/2006 ዓ.ም ድረስ በነበረው ጊዜ የውይይት መድረኮች የተካሄዱት »» ገጽ.4 አቶ ሽፈራው ጃርሶ በበዓሉ ላይ ንግግር ሲያደርጉ የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች የብሔር ብሐረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን በድምቀት አከበሩ የስኳር ኮርፖሬሽን የስራ አመራሮችና ሠራተኞች ስምንተኛውን የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን ህዳር 28 ቀን 2006 ዓ.ም በድምቀት አከበሩ፡፡ “ሕገ መንግስታችን ለሕዳሴያችን” በሚል መሪ ቃል በተከበረው በዚህ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር የኮርፖሬት ሪፎርምና አቅም ግንባታ አማካሪ አቶ አደባባይ በውስጥ ገፆች የስኳር ልማት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ... ገጽ. 15 አባይ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ከመበታተን አደጋ ወጥተው አንድ መሆን የቻሉት የቃል ኪዳን ሰነዳቸው በሆነው ሕገ መንግስት አማካይነት መሆኑን አስታውሰው ፣ ሕገ መንግስቱን በማወቅና በማሳወቅ እንዲሁም እሴቶቹን በመፈጸም ኃላፊነትን መወጣት ይገባል ብለዋል፡፡ የኢፌዴሪ ሕገ መንግስት የሕዝቦችን በጋራ አብሮ የመኖር በጎ ልምዶችን በማጠናከርና »» ገጽ.15 የሳቡሬ ከተማ ከስኳር ልማቱ ተጠቃሚ እየሆነች ነው...ገጽ. 8 አቶ አደባባይ አባይ ጣና በለስ የተቀናጀ የስኳር ልማት ፕሮጀክት ....ገጽ. 19 በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት :+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 A.A Sugar_corp@ethionet.et | www.etsugar.gov.et | www.facebook.com/etsugar
  • 2. ጣፋጭ ዜና መፅሄት የዋና ዳይሬክተሩ መልዕክት ክቡር አቶ ሽፈራው ጃርሶ በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር የአምስት ዓመቱ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የግብርና ምርቶችን በዓይነትና በጥራት የምናሣድግበት ብቻ ሣይሆን ከግብርና ወደ ኢንዱሰትሪ የምናደርገውን መዋቅራዊ ሽግግርም የምናሰፋበትና የምናፋጥንበት ጭምር ነው፡፡ ይህን መዋቅራዊ ሽግግር ተግባራዊ ለማድረግ ከተያዙ ዕቅዶች መካከል የስኳር ልማት ንዑስ ዘርፍ ዋንኛው ነው፡፡ ዘርፉ ግብርናን ከኢንዱስትሪው ጋር በማገናኘት ሰፊ የሥራ ዕድል የሚፈጥር፣ የግብርና ምርታማነትን ለማጎልበት የሚያስችል፣ የቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክህሎት ለማሣደግ የሚያግዝ፣ የአገር ውስጥ የስኳር ምርት ፍላጎት ከመሸፈን አልፎ ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሪ ለማስገኘት የሚያስችል ነው፡፡ በተጓዳኝ በሚመረቱ ምርቶችም የአገሪቷን የኃይል አቅርቦት በመደገፍ፣ ኤታኖልን የመሳሰሉ ከውጭ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚገቡ የነዳጅ ምርቶችን በመቀነስ እና ለሌሎች ኢንዱስትሪዎች ግብዓት የሚሆኑ ምርቶችን በማምረት ዘርፉ ሊያበረክት የሚችለው አስተዋፅኦ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ በቅርቡ የስኳር ልማት ንዑስ ዘርፍ ያለፉትን ሦስት ዓመታት አፈፃፀም ለማየትና በቀሪዎቹ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ትግበራ ጊዜያት የት መድረስ እንደሚቻል ለመረዳት ባካሄድነው ግምገማ ለዕቅድ ዘመኑ ከተቀመጠው ግብ 70 በመቶውን ማሣካት እንደምንችል አይተናል፡፡ በዚሁ መሠረት አዳዲስ ከሚገነቡ ፋብሪካዎች ሰባቱን ማለትም ተንዳሆ አንድን በያዝነው ዓመት እንዲሁም ተንዳሆ ሁለት፣ ኩራዝ አንድ፣ ከሰም፣ በለስ አንድና ሁለት እና አርጆ ዲዴሣ፣ በ2007 ዓ.ም. ተጠናቀው ማምረት ይጀምራሉ፡፡ እነዚህ ወደ ማምረት የሚገቡ ፋብሪካዎች ከፍተኛ የማስፋፊያ ሥራ ከተሰራላቸው ነባር ሦስት ፋብሪካዎች ጋር በድምሩ በ2007 መጨረሻ ከ1.5 ሚሊዮን ቶን ያላነሰ ስኳር ማምረት የሚያስችሉን ይሆናሉ፡፡ በተመሣሣይ በተጓዳኝ የሚመረቱ ምርቶች መጠን፣ በልማት አካባቢዎቹ የሚካሄዱ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትና የመሠረተ ልማት ግንባታ፣ እንዲሁም የሥራ ዕድል ፈጠራና መሰል የልማት እንቅስቃሴዎች ጉልህ በሆነ ደረጃ ያድጋሉ፡፡ በቀጣዩ ዓመት መጨረሻ የምንደርስበት ግብም ሆነ ከዚያ ቀጥሎ ባሉ ቀጣይ ጊዜያት በስኳር ልማት ዘርፍ ልናስመዘግብ የምናስበው ውጤት ከምንም በላይ ምርታማነታችንን በማሣደግ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ በሔክታር ከ1500 ኩንታል ያላነሰ የሸንኮራ ምርት ለማግኘት የሚያስችሉን የመሬት እንክብካቤና የግብዓት አቅርቦት እንዲሁም የጥናትና የምርምር ሥራዎች ላይ አተኩረን እንሰራለን፡፡ የቴክኖሎጂ ዕውቀትና አጠቃቀማችንን በከፍተኛ ደረጃ ለማሻሻልም ትኩረት ሰጥተን እንንቀሳቀሳለን፡ ፡ ጤንነቱ የተጠበቀ፣ ምርታማነቱ የላቀ፣ ሥነ-ምግባሩ የጎለበተ አምራች የሰው ኃይል በኢንዱስትሪው ውስጥ በብዛት እንዲፈጠርም ልዩ ልዩ ተግባራትን እናከናውናለን፡፡ ኢንዱስትሪው ሠላማዊና የተረጋጋ ሆኖ እንዲቀጥል ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ ተግባራትም ይከናወናሉ፡፡ የዚህ ሁሉ ድምር ውጤት ከፍተኛ የስኳርና የተጓዳኝ ምርቶች በማምረት የአገሪቱን ኢኮኖሚ በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ ህዝባችንን እና የዚህ ውጤት ተዋናይ የሆነውን ሠራተኛ የእድገቱ ተጠቃሚ ማድረግ ነው፡፡ በእርግጥ ከፊታችን ያለው ትልቅ ኃላፊነት የሚጠይቅ ተልዕኮ ነው፡፡ የተቋሙ ሥራ አመራር አባላትና ሠራተኞች እንዲሁም በተለያዩ የኮንትራት ሥራዎች ውስጥ የሚሣተፉ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ባለድርሻ አካላት ሁላችንም ልናሣካው የሚጠበቅብንን ትልቅ ተልዕኮ የሚመጥን ምላሽ ለመስጠት በጋራ እንድንረባረብ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ፡፡ 2
  • 3. በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ኮርፖሬሽኑ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን... ኮርፖሬሽኑ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱን የሶስት ዓመታት (2003 - 2005 ዓ.ም ) አፈጻጸም በመፈተሽ በአምስት ዓመቱ የስኳር ልማት እቅድ የት መድረስ እንደሚቻል በትክክል ለማወቅ ባደረገው ግምገማ በአምስት አመቱ የእቅድ ዘመን በስኳር ልማት ዘርፍ ከተቀመጠው የከፍተኛ አማራጭ የግብ ስኬት 70 በመቶውን ማሣካት እንደሚችል አረጋግጧል፡፡ የሚቻልበት ደረጃ ላይ የሚያደርስ ይሆናል፡፡ በአሁኑ ወቅት ኮርፖሬሽኑ አገሪቱ ስኳር ከውጭ ለማስመጣት ታወጣ የነበረውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ማዳን የሚችልበት ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን እንዲያውም በ2007 ዓ.ም ወደ 658,200 ቶን ስኳር ወደ ውጭ በመላክ ከ376 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዓመታዊ የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ አገሪቱ በስኳር ልማት ዘርፍ ያላትን ከፍተኛ እምቅ አቅም በማልማት ተጠቃሚ ለመሆን በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አዳዲስ ፋብሪካዎችን የመገንባትና የነባሮቹን አቅም በከፍተኛ ደረጃ የማሣደግ ዕቅድ ተይዞ ነበር፡፡ ምንም ዓይነት የመሠረተ ልማት አውታሮች ባልነበሩበት፣ ለዘርፉ ልማት የሚውል በቂ ፋይናንስ በሌለበትና የዘርፉ ልምድና የማስፈፀም አቅም ውስን በነበረበት ሁኔታ ሥራው የተጀመረ ከመሆኑ አኳያ ሲታይ አሁን የተደረሰበት ውጤት እጅግ ተስፋ ሰጪ ነው፡፡ በቀሪዎቹ የትግበራ ጊዜያት የመስኖ ልማት ግንባታን አጠናክሮ በመቀጠልና በፕሮጀክቶች 149,790 ሔክታር አገዳ በመትከል በአጠቃላይ የፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች የአገዳ ሽፋንን ከ204,000 ሄክታር በላይ ለማድረስ ጥረት ይደረጋል፡፡ የማስፋፊያ ስራ በተጠናቀቀላቸው በነባር ስኳር ፋብሪካዎችና በአዳዲስ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች አማካኝነት በ2006 እና በ2007 ዓ.ም ከ92 ሺህ በላይ ተጨማሪ የሥራ ዕድሎች ይፈጠራሉ፡ በመሆኑም ሥራው ሲጀመር በነበረው በዚህ ፡ የልማቱ ሥራ በሚካሔድባቸው አካባቢዎች አስቸጋሪ ሁኔታ የከፍተኛውን የግብ ስኬት የሚገኘው ሕብረተሰብም በፕሮጀከቶቹ አማካኝነት አማራጭ 70 በመቶ መድረስ ከተቻለ በቀጣይ ከሚፈጠሩ የስራ ዕድሎች በቀጥታና በተዘዋዋሪ አጭር ሊባል በሚችል ጊዜ ውስጥ በስኳር ልማት ተጠቃሚ የሚሆንበት አቅጣጫም ተቀምጧል፡፡ ከዓለም ግንባር ቀደም ስኳር አምራች አገሮች ተርታ መሰለፍ እንደሚቻል አሁን የተደረሰበት ውጤት ከስኳር ምርት በተጓዳኝ በእቅድ ዘመኑ መጨረሻ አመላክቷል፡፡ ከስኳር ፋብሪካዎቹ 197 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ላይ እንደሚደረስ ኮርፖሬሽኑ እያካሄዳቸው ካሉ የስኳር ፋብሪካ ይገመታል፡፡ ከዚህም ባሻገር በ2007 የኢታኖል ግንባታዎች መካከል የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ምርትን ከ134 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ በማድረስ የመጀመሪያ ምዕራፍ በማጠናቀቂያ ሂደት ላይ አገሪቱ ለነዳጅ የምታወጣውን ወጪ ለመቀነስ የሚገኝ ሲሆን፣ በዚህ የበጀት ዓመት ወደ ማምረት ኮርፖሬሽኑ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ ይሸጋገራል፡፡ የበለስ 1 እና 2፣ የኩራዝ 1፣ የተንዳሆ 2፣ የከሰምና የአርጆ ዲዴሳ ፋብሪካዎች ደግሞ ኮርፖሬሽኑ በ2006 እና በ2007 በቁጥር 3,265 በ2007 ማምረት ይጀምራሉ፡፡ በማስፋፊያ የመኖሪያ ቤት፣ የአገልግሎት መስጫና ተያያዥ ፕሮጀክቶችም በኩል ወንጂ ሸዋና ፊንጫአ ስኳር ግንባታዎችን አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃትም ፋብሪካዎች ተጠናቀው ተጨማሪ ምርት በመስጠት በመረባረብ ላይ ነው፡፡ ላይ ናቸው፡፡ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የስኳርና በእስካሁን የልማት ጥረት ዓመታዊ የሀገር ውስጥ ተጓዳኝ ምርቶች ግብ ተደራሽነት ፍኖተ ካርታ የስኳር ምርት በ2005 መጨረሻ ከነበረበት 232 (Road Map) በጥቅምት ወር ተዘጋጅቶ በሥራ ሺህ ቶን ተከታታይ ዕድገት በማስመዝገብ በ2007 ላይ ውሏል፡፡ ፍኖተ ካርታው በስኳርና ተጓዳኝ መጨረሻ ከ1 ሚሊዮን 585 ሺህ ቶን በላይ ምርቶች ኢንዱስትሪ ልማት ንዑስ ዘርፍ ውስጥ እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡ ይህም የአገር ውስጥ በ2006 እና በ2007 ዓ.ም ተፈጻሚ የሚሆኑ ዋና ፍጆታ ከመሸፈን አልፎ ምርቱን ወደ ውጭ መላክ ዋና ግቦችን አካቷል፡፡ 3
  • 4. ጣ የሸንኮራ አገዳሄ ት ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ አብቃይ በምስራቅ ሸዋና አርሲ ዞኖች በሚገኙና የሸንኮራ አገዳ ልማቱ በሚካሄድባቸው ወረዳዎችና ቀበሌዎች ከተውጣጡ በየደረጃው ከሚገኙ አመራር አካላት፣ የሸንኮራ አገዳ አብቃይ አርሶ አደሮችና ህብረት ሥራ ማህበራት ተወካዮች ጋር ነው፡፡ ህዳር 14 /2006 ዓ.ም. በአዳማ ገልማ አባገዳ የስብሰባ አዳራሽ ለስድስት ቀናት በተለያዩ ደረጃዎች ሲካሄድ የቆዩ ውይይቶች የማጠቃለያ መድረክ የተዘጋጀ ሲሆን፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ አብዱላዚዝ መሐመድ፣ የክልሉ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት፣ የፌዴራል ህብረት ስራና ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የስራ ኃላፊዎች፣ የስኳር ኮርፖሬሽን የስራ ኃላፊዎች፣ የሸንኮራ አገዳ አብቃይ አርሶ አደር ማህበራት አመራሮች፣ ከየአካባቢዎቹ የመጡ አርሶ አደሮች፣ የምሥራቅ ሸዋና የአርሲ ዞኖች አስተዳዳሪዎችና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የአዳማ፣ የቦሰትና የዶዶታ ወረዳዎች አመራሮችና ሌሎች የሚመለከታቸው 581 ተሳታፊዎች በማጠቃለያ መድረኩ ላይ ተገኝተዋል፡፡ የስኳር ኮርፖሬሽን የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳመነ ዳሮታ በውይይቱ ላይ “በወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ እና በሸንኮራ አገዳ አብቃይ አርሶ አደር ማህበራት (አውትግሮወርስ) መካከል የሚታየው የልማት አፈጻጸም፣ ተግዳሮቶችና ኪራይ ሰብሳቢነት” በሚል ርእስ የመወያያ ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡ አቶ ዳመነ ባቀረቡት ጽሁፍ የአገዳ መሸጫ ዋጋ ሳይሻሻል መቆየቱ፣ የተሟላ የመሰረተ ልማት እጥረት፣ ለሸንኮራ አገዳ እድገት የሚበጁ እንክብካቤዎች ወቅታቸውንና ጥራታቸውን ጠብቀው ባለማከናወናቸው ምክንያት የሚከሰት የምርታማነት ማነስ፣ ከልማቱ ጋር የሚጣጣም የስራ ባህል አለመኖር፣ በአንዳንድ ማሳዎች ላይ ወቅቱን ጠብቆ መሬቱን አለማዘጋጀት፣ በቂ የሆነ የመስኖ ውኃ አለማቅረብ፣ የመድን ሽፋን 4 ህብረት ሥራ ማህበራት ከወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ጋር ... አለመኖርና ሌሎችንም ተያያዥ ችግሮች ጠቅሰዋል፡፡ በተጨማሪም በዩኒየን አመራር፣ በመሰረታዊ ማህበራት አመራርና በፋብሪካው በኩል የሚንጸባረቁ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባራት እንዲሁም የአሰራርና የአደረጃጀት ክፍተትም እንደችግር ተነስተዋል፡፡ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በጽሁፋቸው ማጠቃለያ በመፍትሔነት ከጠቀሱዋቸው ሐሳቦች መካከል የኪራይ ሰብሳቢነት ትግሉን በቀጣይነት አጠናክሮ መቀጠልና ግልጽነት ያለው አሰራርና ድጋፍ አሰጣጥ ማስፈን፣ የአቅም ግንባታ ስራዎችን ማጠናከር፣ አሰራርን ማሻሻል፣ የመድን ሽፋን እንዲኖር ማድረግ፣ የባለድርሻ አካላት ድጋፍና ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር የሚሉትና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ በውይይቱ ወቅት የሸንኮራ አገዳ አብቃይ አርሶ አደር ማህበራት አመራሮችና አባላት መፍትሔ ያሻቸዋል ያሉዋቸውን ጉዳዮች አንስተዋል፡፡ ከነዚህም መካከል ለፋብሪካው ለሚያቀርቡት የሸንኮራ አገዳ ምርት ዋጋ ይሻሻል፣ ከመስኖና ከሌሎች የምርት ግብአቶች አቅርቦት ጋር በተያያዘ ፈጣን አገልግሎት የሚሰጥበት መንገድ ይመቻች፣ በማቆያ የተያዙ መሬቶች ቶሎ ወደ ልማት ይግቡ የሚሉና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችም ይገኙበታል፡፡ የኮርፖሬሽኑ ተወካዮች የውይይት መድረኩ በሸንኮራ አገዳ አብቃይ አርሶ አደሮች ማህበራትና ፋብሪካው እንደ ችግር የሚያነሷቸውን ጉዳዮች በመለየት ሁሉንም ተጠቃሚ በሚያደርግ አኳኋን ለማስተናገድ የተመቻቸ መሆኑን ገልፀዋል፡ ፡ ስኳር ለማምረት ብዙ ግብዓቶች ጥቅም ላይ እንደሚውሉ የገለጹት የኮርፖሬሽኑ ተወካዮች ይህንን ታሣቢ ያደረገ የዋጋ ድርድር ለማካሄድ ጭምር መድረኩ መመቻቸቱን አስረድተዋል፡፡ በአገልግሎት አቅርቦት ረገድ አሉ የተባሉ ችግሮችን ለመፍታትም ፋብሪካው ያላሰለሰ ጥረት እንደሚያደርግ አብራርተው በተመሣሣይ ከአርሶ አደሮች በኩል ከምርታማነትና ፋብሪካውን እንደ አገርና እንደራሣቸው ሐብት አድርጎ በመቁጠር ረገድ ያሉ የአመለካከት ችግሮች እንዲስተካከሉ አሳስበዋል፡፡ በቀጣይም ፋብሪካውና ማህበራቱ በመደበኛ ሁኔታ በመወያየት ሁለቱንም አካላት ተጠቃሚ የሚያደርግ አቅጣጫን መከተልና ለጋራ ልማት አብረው መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ መድረኩን የመሩት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ም/ርዕሰ መስተዳድሩ በሰጡት የማጠቃለያ ሐሣብ በአገሪቱ ልማት ውስጥ ትልቅ ስፍራ ላለው የስኳር ልማት መሳካት የምስራቅ ሸዋና የአርሲ ዞኖችና የየወረዳዎቹ አመራሮች እንዲሁም የፋብሪካውና የማህበራትና የዩኒየኖች አመራሮችና ሰራተኞች ተቀናጅተው እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡ ም/ርዕሰ መስተዳድሩ ህብረተሰቡም ፋብሪካው እራሱንም ሆነ አገሪቱን በከፍተኛ ደረጃ የሚጠቅም መሆኑን ተረድቶ የባለቤትነት ስሜትን እንዲያዳብር በማሳሰብ የሁለቱ ግንኙነት በግልጽነትና በፈጣን አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተመሰረተ መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡ ለዚህም ስኬት የውይይት መድረኮች በመደበኛነት ተጠናክረው እንደሚካሄዱ ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፣ የስራ ኃላፊዎች፣ የሸንኮራ አገዳ አብቃይ አርሶ አደር ማህበራት አመራርና አባላት፣ የዩኒየን አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም የፋብሪካው አመራሮችና ሰራተኞች ተወካዮች ሁሉንም ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ ተቀናጅተው ለመስራት ባለ ስድስት ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል፡፡ በአቋም መግለጫቸውም የስኳር ልማቱ የአርሶ አደሩን ኑሮ ለመለወጥና ለሀገር ልማትም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው በመገንዘብ ለውጤታማነቱ እጅ ለእጅ ተያያይዘው ለመስራትና የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በውይይት እየፈቱ ለመሄድ የየበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ አረጋግጠዋል፡፡ በማህበራቱና በፋብሪካው መካከል ውይይት በተደረገበት ወቅት
  • 5. በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ የዓለም ኤድስ ቀን በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ በተከበረበት ወቅት የዓለም ኤድስ ቀን በአገር አቀፍ ደረጃ በመተሐራ... በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ፣ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብድላዚዝ መሐመድና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች ለሚመሩ ስኳር ኮርፖሬሽንን ለመሳሰሉ ተቋማት ኤች.አይ.ቪ ኤድስን መከላከልና መቆጣጠር ተልዕኮን ከማሳካት ጋር ጥብቅ ቁርኝት አለው ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ሙላቱ በበዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግር በመላ አገሪቱ በተፈጠሩ በብዚ ሺ የሚቆጠሩ አምራች ኃይሎች በሚንቀሳቀሱባቸው ታላላቅ የልማትና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ስርጭትን መግታት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡ ኮርፖሬሽኑ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ የሚገኝባቸውን 2100 ሠራተኞችንና በበሽታው ወላጆቻቸውን ያጡ ሕጻናትን ከመደገፍና ከመንከባከብ በተጓዳኝ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የተለያዩ የመከላከል ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ የሚገኝባቸው ወገኖች የጸረ-ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መድኃኒት አግኝተው አምራች ኃይሎች እንዲሆኑና በአገራቸው የልማትና የእድገት ጉዞ ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ ማገዝና መርዳት አስፈላጊ ነውም ብለዋል ፕሬዚዳንት ሙላቱ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በመከላከልና በእንክብካቤ ስራው ውስጥ ጉልህ ሚና የሚጫወት የኤች.አይ.ቪ ግብረ ኃይል መቋቋሙንና ከተቋሙ አመታዊ በጀት ላይ ሁለት በመቶ የሚሆነው ለዚሁ ስራ እንዲውል መመደቡንም አብራርተዋል፡፡ በዓሉ የተከበረበት የመተሐራ ስኳር ፋብሪካን በመሳሰሉና በመገንባት ላይ ባሉት ታላላቅ ፕሮጀክቶችና በተለያዩ የልማት ተቋሞች በመስራት ላይ የሚገኙ ወጣቶች ከኤች.አይ.ቪ./ኤድስ ራሳቸውን መጠበቅ ቀዳሚ ተግባራቸው ሊሆን እንደሚገባ ፕሬዚዳንቱ አሳስበዋል፡፡ በእስካሁኑ ጅምር የመከላከል፣ የመንከባከብና ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች አበረታች ውጤቶች ቢመዘገቡም የስኳር ልማት ዘርፉ ካለው ተጋላጭነትና የተያዘውን እቅድ በአጭር ጊዜ ለማሳካት ከፍተኛ ጥረት የሚጠይቅ ከመሆኑ አንጻር ኮርፖሬሽኑ የበለጠ መስራት የሚጠበቅበት መሆኑንም አቶ ሽፈራው ጠቁመዋል፡፡ በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ በበኩላቸው ከስራቸው ባሕሪ የተነሳ በርካታ የሰው ኃይል የሚሰማሩባቸውን የዓለም ኤድስ ቀን በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ መከበሩ ኮርፖሬሽኑ የቫይረሱን ስርጭት በመግታት ረገድ የተለየ ኃላፊነት እንዲሸከም የሚያደርግ መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ ለዚህም በዋና መስሪያ ቤት ፣ በፋብሪካዎችና በፕሮጀክቶች የተሰማሩ ሰራተኞች የቫይረሱን ስርጭት በመከላከል በስኳር ልማት ዘርፍ የተቀመጡ የልማት ግቦችን ለማሳካት በበለጠ ቁርጠኝነት እንዲነሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር ከሰተብርሀን አድማሱ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ኤች.አይ.ቪ./ኤድስን በመከላከል ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገቡ ከሚገኙ 16 የአፍሪካ አገሮች መካከል ግንባር ቀደም መሆን መቻሏን አስታውቀዋል፡፡ በቀጣይም ሕዝብ በብዛት በሚገኝባቸው የታላላቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የተጠናከረ የመከላከል ስራ እንደሚሰራ ይፋ አድርገዋል፡፡ ኢትዮጵያ በኤች.አይ.ቪ የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር በ90 በመቶ እንዲሁም በቫይረሱ ምክንያት ይደርስ የነበረውን ሞትና ጉዳት ከ54 በመቶ በላይ መቀነስ መቻሏ በበዓሉ ላይ ይፋ ተደርጓል፡፡ በአገር አቀፍ ደረጃ በዓሉ የተከበረበት የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ባቋቋመው አንድ ሆስፒታል ፣ ሁለት ፖሊና አራት ሳተላይት ክሊኒኮች አማካይነት ለፋብሪካው ሰራተኞች ፣ ቤተሰቦቻቸውና ለአካባቢው ነዋሪ ሕብረተሰብ የኤች.አይ.ቪ. ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ስራ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ 5
  • 6. ጣፋጭ ዜና መፅሄት አዲሱ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብካ የወንጂ ሸዋና የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካዎች በከፍተኛ የማምረት አቅም ሥራ ጀመሩ የማስፋፊያ ሥራቸው የተጠናቀቀው የወንጂ ሸዋና የፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካዎች ከጥቅምት ወር 2006ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ በተሳካ ሁኔታ ሥራ ጀመሩ፡፡ የተካሄደው የማስፋፊያ ሥራ የፋብሪካዎቹን የማምረት አቅም በከፍተኛ ደረጃ ያሳድገዋል፡፡ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ስራው የተጠናቀቀው የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ የማምረት አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ ከጥቅምት 10/2006 ዓ.ም ጀምሮ እያመረተ ነው፡፡ ፋብሪካው በ2006 በጀት ዓመት 2 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ያመርታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ይህ የምርት መጠን በ2005 በጀት ዓመት ከተገኘው ምርት ጋር ሲነጻጸር የ900 ሺህ ኩንታል ልዩነት ይኖረዋል፡፡ ፋብሪካው በሂደት በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር በአመት ወደ 2 ሚሊዮን 700 ሺህ ኩንታል ስኳር ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በተመሳሳይ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ 6 ዕድሜ አገልግለው ስኳር ማምረት ባቆሙት ነባሮቹ የወንጂ እና የሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች ምትክ በተከናወነ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ግንባታው የተጠናቀቀው አዲሱ ዘመናዊ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ከጥቅምት 22/2006 ዓ.ም ጀምሮ ስኳር ማምረት ጀምሯል፡፡ በ2005ዓ.ም መጨረሻ የሙከራ ምርት ያካሄደው ይህ ፋብሪካ በያዝነው በጀት ዓመት ከ950 ሺህ ኩንታል በላይ ስኳር እንዲያመርት የታቀደ ሲሆን፣ ለምርቱ የሚሆን በቂ የሸንኮራ አገዳና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶች ዝግጁ ሆነዋል፡፡ በሌላ በኩል በያዝነው በጀት ዓመት 1 ሚሊዮን 300 ሺህ ኩንታል ስኳር እንደሚያመርት የሚጠበቀው የመተሃራ ስኳር ፋብሪካ ስራ የጀመረ ሲሆን፣ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካም በያዝነው በጀት ዓመት ምርት ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በተጠቀሱት አራት የስኳር ፋብሪካዎች በበጀት ዓመቱ ከ5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ስኳር ለማምረት የታቀደ ሲሆን፣ ይህም ከአምናው ምርት ጋር ሲነጻጸር ከእጥፍ በላይ ይሆናል፡፡ በዘርፉ ዘንድሮ የሚገኘው ምርት የአገር ውስጥ የስኳር ፍላጎትን ከማሟላት አሮጌዎቹ የወንጂ እና የሸዋ ስኳር ባለፈ ምርቱን ከውጭ ለማስገባት ይወጣ ፋብሪካዎች በዓመት 750 ሺህ ኩንታል የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ሙሉ በሙሉ ስኳር ያመርቱ የነበረ ሲሆን፣ በምትካቸው ያስቀራል፡፡ የተገነባው አዲሱ ፋብሪካ የመጀመሪያ ምዕራፉ ብቻ በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምር የፋብሪካዎቹ የማምረት አቅም እንዲያድግና በዓመት ከ1 ሚሊዮን 460 ሺህ ኩንታል የአመቱ የማምረት ተግባር ውጤታማ በሆነ በላይ ስኳር የማምረት አቅም ይኖረዋል፡፡ መልኩ እንዲጀመር አመራሮችና ሠራተኞች ሰፊ ርብርብ አድርገዋል፡፡
  • 7. በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ጎበኙ ሰራተኞቹ በግድቡ የግንባታ ሂደትና በተመለከቱት ነገር ደስተኛ ሆነዋል የስኳር ኮርፖሬሽን ሠራተኞች “ከስኳር ልማቱ ጎን ለጎን ለግድቡ ስኬት እንተጋለን!” የሚል መሪ ቃል አንግበው በሁለት ዙሮች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ጎበኙ፡፡ ሠራተኞቹ የኮርፖሬሽኑ የማህበራዊ ጉዳዮች በሚያስተባብረው የአገርህን እወቅ ክበብ አማካኝነት ግድቡ በሚገነባበት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ተገኝተው ጉብኝት ያካሄዱት ጥቅምት 4 እና ህዳር 9 ቀን 2006 ዓ.ም ነው፡፡ በመጀመሪያው ዙር 41 የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ከጥቅምት 2 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ቀናት ግንባታው በሚካሄድበት ስፍራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፣ ከህዳር 9 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በተደረገው የሁለተኛው ዙር ጉብኝት ደግሞ 35 ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል ፡፡ በሁለቱም ዙሮች ግድቡ ወደሚገነባበት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ ላመሩት የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ስለ ግድቡ ግንባታና ተያያዥ ጉዳዮች በከፍተኛ የፕሮጀክቱ ባለሙያዎች በአዳራሽ ውስጥና በመስክ ጉብኝት ሰፊ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡ በጉብኝቶቹ ወቅት በሥራ ምክንያት በግንባታው ስፍራ መገኘት ያልቻሉት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ለኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ባስተላለፉት የጽሁፍ መልዕክት “በቅድሚያ የራሳችሁን ፕሮጀክት ስለጎበኛችሁ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ፡፡ በተመለከታችሁት ሁሉ ደስተኛ እንደሆናችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በቀጣይ ሁላችንም በከፍተኛ የአገር ፍቅር እጅ ለእጅ በመያያዝና የተጀመረውን የልማት ጉዞ ይበልጥ በማስቀጠል በኢኮኖሚ የበለጸገች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ በየተሰማራንበት የስራ መስክ ሁሉ ጠንክረን መስራት ይጠበቅብናል ” ብለዋል፡፡ የግድቡን ግንባታ አስመልክቶ አንዳንድ ያነጋገርናቸው ተጓዦች በሰጡን አስተያየት በቴሌቪዥን መስኮት ብቻ ይመለከቱት የነበረውን የግድቡን ሥራ በአካል ተገኝተው መመልከታቸው የበለጠ የባለቤትነት ስሜትና በቁጭት የመስራት ተነሳሽነትን እንደፈጠረላቸው ገልጸው፣ ለግንባታው ስኬት የጀመሩትን አስተዋጽኦ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡ የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ከግድቡ በተጨማሪ በአሶሳ ከተማ የሚገኙትን የሼህ ሆጀሌ አልሃሰን የችሎት አዳራሽና የመቃብር ስፍራ ጎብኝተዋል፡፡ በሦስት ዙሮች ተከፍሎ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የጉብኝት መርሐ ግብር ለሦስተኛው ዙር ጉዞ ቅድመ ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ »» ገጽ.8 7
  • 8. ጣፋጭ ዜና መፅሄት የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች... ወደ ታላቁ የህዳሴ ግድብ የጉዞ መርሃ ግብሩን ያዘጋጀው የኮርፖሬሽኑ የአገርህን እወቅ ክበብ ጥቅምት 23 ቀን 2005 ዓ.ም ተቋቁሞ እስካሁን 117 አባላትን ያቀፈ ሲሆን፣ ዓላማው ሠራተኞችን ከማዝናናትና ግንዛቤ ከማስጨበጥ ባለፈ መንግሥት በሚያካሂደው ዘላቂ ልማት ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ማስቻል ነው፡፡ በተመሳሳይ ዜና የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ 39 ሠራተኞች፣ የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት 300 ሠራተኞች እንዲሁም የሳቡሬ ከተማ ከስኳር ልማቱ ተጠቃሚ እየሆነች ነው ስያሜዋን ከአንድ ፈረንሳዊ ባለሀብት የወረሰችው የሳቡሬ ከተማ የስኳር ልማቱን ተከትሎ ከተዘረጉ መሠረተ ልማቶች ተጠቃሚ መሆኗ ተገለጸ፡፡ በ1904 ዓ.ም እንደተቆረቆረች የሚነገርላት ይህች ከተማ የከሠም ስኳር ልማት ፕሮጀክትን ተከትለው በተዘረጉ የመንገድ ፣ የተንቀሳቃሽ ስልክ፣ የገመድ አልባ የብሮድባንድ ኢንተርኔትና የ24 ሰአት የመብራት አገልግሎቶች ተጠቃሚ መሆን ችላለች፡፡ ከተማዋ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ለከሰም ስኳር ልማት ተብለው በተዘረጉ የተለያዩ የመሠረተ ልማት ስራዎች ተጠቃሚ መሆኗ ለእድገቷ አስተዋጽዖ በማበርከት ላይ እንደሚገኝ ተመልክቷል፡፡ የፊንጫአ ሰራተኞች በጉዞ ላይ የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ 42 ሠራተኞች የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሥራ እቅስቃሴን ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ ስለ ግድቡ ፕሮጀክት አጠቃላይ እንቅስቃሴ በመረዳታቸው መደሰታቸውን የገለጹት ሠራተኞቹ ለፕሮጀክቱ የሚያደርጉትን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር በተሰማሩበት ዘርፍ ተልዕኮአቸውን በላቀ ሁኔታ በመፈጸም አገሪቱ ወዳለመችው የእድገት ደረጃ እንድትደርስ በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁነታቸውን ገልጸዋል፡፡ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማትን ተከትላ የተመሠረተችውና በኋላም የላይኛው አዋሽ አግሮ ኢንዱስትሪ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ሳቢያ የተስፋፋችው ሳቡሬ የገጠር ከተማ ስትሆን ለበርካታ አመታት በቂ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት አልነበሯትም፡፡ ከተማዋ የዘመናዊ የግንኙነት መረቦች ተጠቃሚ መሆኗ እንደ ዳግም ልደት እንደሚቆጠርና በቀጣይ በፍጥነት እድገት ለማስመዝገብ በምታደርገው ጥረት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንደሚኖረው የከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል የላከልን ዘገባ አመልክቷል፡፡ በአንድ ቀን ከ 74 ሄክታር በላይ የሸንኮራ አገዳ ዘር ተተከለ በጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በሰራተኞች በተደረገ የተቀናጀ ንቅናቄ በአንድ ቀን 74 ነጥብ 8 ሄክታር መሬት በሸንኮራ አገዳ ዘር መሸፈኑ ተገለጸ፡፡ በመከፋፈሉና ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶችን በማድረጉ ሰራተኛው በእለቱ በተከላ ስራው ላይ ብቻ እንዲያተኩር ተደርጎ ተፈላጊው ውጤት ሊገኝ ችሏል፡፡ በአገዳ ተከላ የንቅናቄ እቅድ ዙሪያ የፕሮጀክቱ አመራር ከሰራተኛው ጋር ባደረገው እንቅስቃሴ “ሁሉም መንገዶች ወደ በለስ አገዳ ተከላ ያመራሉ!” በሚል መሪ ቃል ወደ ተግባር ተገብቶ አበረታች ውጤት መመዝገቡን የፕሮጀክቱ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ያደረሰን መረጃ ያመለክታል ፡፡ ለስራው የሚያስፈልገውን ተጨማሪ የሰው ኃይል ከአማራና ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ከማቅረብ በተጨማሪ የአገዳ አቅርቦት ችግር እንዳይኖር ያሉትን የፕሮጀክቱንና በኪራይ የተገኙትን ተሽከርካሪዎች በአግባቡ መጠቀም በመቻሉ እቅዱ ከግብ ደርሷል፡፡ በሌላ በኩል ሁኔታውን በቅርብ ይከታተል የነበረው ከ3ዐዐዐ በላይ የሚሆን የጃዊ ወረዳ ህዝብ ፣ የንግዱ ማህበረሰብና የወረዳው የፖሊስ አባላት የሰራተኛውን ሞራልና መነሳሳት በመደገፍ የሁለት ቀናት የአገዳ ተከላ ዘመቻ ሥራ ማከናወናቸውን የፕሮጀክቱ የህዝብ ግንኙነት ክፍል የላከው መረጃ ያመለክታል ፡፡ የልማት ቡድኖችን በአራት የዞን ጽ/ቤቶች ከፋፍሎ ስራን ቆጥሮ በመስጠትና በቡድኖቹ መካከል ከፍተኛ የሆነ የሥራ ውድድር መንፈስ በመፍጠር ውጤቱ ሊገኝ መቻሉን ነው መረጃው የጠቆመው፡፡ የፕሮጀክቱ የአመራር ኮሚቴ ወረዳዎችን 8
  • 9. በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ በላይ መድቦ እርጅና የተጫናቸው ማሽነሪዎች እንዲሻሻሉና ለጥገና የሚያስፈልጉ ግብዓቶችም በወቅቱ ከውጭ ሀገሮች እንዲገቡ በመደረጉ ለጥገናው መፋጠን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ አጠቃላይ እድሳት በስኬት ተጠናቀቀ ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦለት ሲከናወን የቆየው የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ አጠቃላይ የእድሳት ሥራ ከተቀመጠለት ዕቅድ አስቀድሞ በስኬት ተጠናቀቀ፡፡ የፋብሪካው ሠራተኞች ጥቅምት 29 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ባካሄዱት የሦስት ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ላይ እደተመለከተው በስኳር ኮርፖሬሽን፣ በፋብሪካው አመራሮችና አጠቃላይ ሠራተኞች በተደረገው ከፍተኛ ርብርብ ለ14 ሳምንታት ሲካሄድ የቆየው ጥገና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቆ ስኳር ማምረት ተጀምሯል፡፡ ፋብሪካውን ለማደስ በተካሄዱ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችና ለሠራተኛው በአመለካከት፣ በመልካም ግንኙነትና በቡድን ግንባታ በተሰጡ ሥልጠናዎች በአመራሩ እንዲሁም በአጠቃላይ ሠራተኛው ዘንድ የባለቤትነት፣ የቁጭት፣ የተነሳሽነትና የቁርጠኝነት ስሜቶች በመፈጠራቸው በጥገናው ሂደት ላይ የታየው ርብርብ እጅግ ከፍተኛ እንዲሆን አስችሎታል፡፡ የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘነበ ይማም በግምገማው ወቅት እንደገለጹት መንግስት ለፋብሪካው እድሳትና ጥገና በሰጠው ልዩ ትኩረት ከ4ዐዐ ሚሊዮን ብር ፋብሪካው ከቀድሞ በተለየ ሁኔታ እንዲጠገን መደረጉን የገለጹት ዋና ሥራ አስኪያጁ በስራው ላይ በተለይም ሠራተኛው ለተጫወተው ከፍተኛ ሚና ታላቅ ክብር የሚገባው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በጥገናው ላይ መላው ሰራተኛ ለ14 ሳምንታት ያህል ከመደበኛ ስራው ውጭ በየዕለቱ ተጨማሪ የአንድ ሰዓት ነጻ አስተዋጽኦ ያበረከተ ሲሆን በዚህም ሰራተኛው 4.5 ሚሊዮን ብር ወጪ ማዳኑ ታውቋል፡፤ በግምገማው ላይ የተሳተፉት ሠራተኞች በበኩላቸው በጥገና ሂደቱ ከመንግሥት ጀምሮ በተዋረድ እስከ ፋብሪካው ከፍተኛ አመራሮች ድረስ የተሰጠው የቅርብ ድጋፍና ክትትል ለስኬት እንዳበቃቸው ተናግረዋል፡፡ እንደ ተሳታፊዎቹ አስተያየት ቁርጠኛ የለውጥ አመራር በመኖሩና ቀደም ሲል የነበሩ የአመለካከት ክፍተቶች እየተለወጡ በመሆናቸው ውጤታማ ተቋማዊ ለውጦችን መመልከት ተችሏል፡፡ የለውጥ ንቅናቄው በፋብሪካ ብቻ ሳይወሰን በመኖሪያ አካባቢዎችም ጭምር በመሆኑ ከፍተኛ የባለቤትነት ስሜት በመፈጠሩ በቀጣይም የተጀመረውን ተቋማዊ ለውጥ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተሳታፊዎቹ መግለጻቸውን የዘገበው የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሕዝብ አደረጃጀት፣ ሕዝብ ግንኙነትና ማህበራዊ ጉዳዮች ክፍል ነው፡፡ ፕሮጀክቱ አመታዊ እቅዱን ለማሳካት እየሰራ ነው የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የ2006 የበጀት አመት እቅድ ትግበራ ዝግጅቱን ከቀሪ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ጋር የተጣጣመ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገለጸ፡፡ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሲሳይ አስራት እንደገለጹት የፕሮጀክቱ የፋብሪካ ግንባታ ስራ እየተጠናቀቀ የሚገኝ በመሆኑ ከዴዴሳ ወንዝ ውሃ በቀጥታ በመሳብ እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ ስድስት ሺ ሄክታር መሬት ላይ ሸንኮራ አገዳ ለመትከልና ፋብሪካውን በማሟሸት ምርት ለመጀመር እየሰራን ነው ብለዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ይህን እቅዱን ለማሳካት በሁለት ሺ ሄክታር መሬት ላይ ሸንኮራ አገዳ ለማልማት የመስኖ ዝርጋታ ለማከናወን የሚያስችል ጨረታ አውጥቶ ጨረታው በሂደት ላይ የሚገኝ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡ በተያያዘም ለልማቱ ከሚፈለገው መሬት ላይ ተነሺ ለሆኑ ዜጎች የማሕበራዊ ተቋማት ግንባታ ለማስፈጸም ከአካባቢው አስተዳደር አካላት ጋር በመሆን እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሚገኝ ዋና ስራ አስኪያጁ አመልክተዋል፡፡ »» ገጽ.12 9
  • 10.
  • 11. የስኳር ኮርፖሬሽን በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 192/2003 ከተቋቋመ ጀምሮ ላለፉት ሦስት አመታት ኮርፖሬሽኑን በሚኒስትር ማዕረግ በዋና ዳይሬክተርነት የመሩት የአቶ አባይ ጸሐዬ ሽኝትና ከጥቅምት 2006 ዓ.ም ጀምሮ በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት የአቶ ሽፈራው ጃርሶ አቀባበል ሥነ ስርአት 11
  • 12. ጣፋጭ ዜና መፅሄት ስልጠና ተከታትለው የተመለሱ ባለሙያዎች ልምዳቸውን አካፈሉ ስልጠናውን ተከታትለው የተመለሱ ባለሙያዎቸ በስኳር ኢንደስትሪ ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ የሞሪሽየስ ተመራማሪዎችና ባለሙያዎች ያላቸውን ዕውቀት፣ ልምድና ተሞክሮ ወደአገራችን መጥተው የሚያካፍሉበት ሁኔታ ቢመቻች አገሪቱ ተጠቃሚ ልትሆን እንደምትችልም ገልጸዋል ፡፡ ሰልጣኞቹ በስልጠናው ወቅት ላገኙት እውቀት፣ ልምድና ተሞክሮ እውቅና የሚሰጥ የምስክር ወረቀት ከምርምርና ስልጠና ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ከአቶ ዮሐንስ መኳንንት እጅ ተረክበዋል፡፡ በሌላ በኩል በሙከራ ማሳ ላይ የሚገኙትና የምርምር ስራቸው ተጠናቆ ለተጠቃሚ ለማድረስ የቴክኒክና የማኔጅመንት ክህሎት ያለው የዘር ማባዛት ስራ እየተሰራላቸው የሚገኙት N52 የሰው ሃይል ለማፍራት የሚያደርገውን ጥረት 219 እና N53 216 የተባሉት ዝርያዎች ተስፋ ሰጪ ውጤት እያሳዩ እንደሚገኙ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ያግዛል፡፡ ጨምሮ አስታውቋል፡፡ ሰልጣኞቹ ለሌሎች ተመራማሪዎች ከስልጠናው ያገኙትን ልምድ ባካፈሉበት ምርምሩን በመሪነት እያካሄዱ የሚገኙት አቶ ወቅት ስልጠናውን በወሰዱበት አገር ምርምር አብይ ጌታነህ ዝርያዎቹ በአገዳ ብዛት፣ በስኳር የሚሰራው በግለሰቦች ፍላጎት ሳይሆን ይዘታቸውና በሄክታር በሚሰጡት የምርት መጠን የደንበኞችን ፍላጎት በመለየትና ችግሮችን በአሁኑ ወቅት በፋብሪካዎች ምርት ላይ ከሚገኘው ለመፍታት ታስቦ በሚቀረጹ ፕሮጀክቶች B52 298 ከተባለው ጋር ሲነጻጸር የተሻሉ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ አክለውም ዝርያዎቹን አማካይነት ነው ብለዋል፡፡ በሰፊው ወደ ተጠቃሚው ለማድረስ ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡ ስልጠናው ትኩረት ካደረገባቸው መስኮች አንዱ የኬን ፋርም ማኔጅመንት ይገኝበታል በሞሪሽየስ ለአንድ ወር በኬን ፋርም ማኔጅመንት ፣ በኢሪጌሽን ፣ በሜካናይዜሽን፣ በኬሚካል ኮንትሮልና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ስልጠና ወስደው የተመለሱ የኮፖሬሽኑ የምርምርና ስልጠና ዘርፍ ባለሙያዎች ከስልጠናው ያገኙትን ልምድ ለተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ባልደረቦች አካፈሉ፡፡ ፋብሪካው ለዜና መጽሔት ዝግጅት ክፍላችን በላከው መረጃ እንዳመለከተው ስልጠናው ኮርፖሬሽኑ የጀመራቸውን የስኳር ልማት ስራዎች በላቀ ደረጃ ለማከናወን የሚያስችል ፕሮጀክቱ አመታዊ እቅዱን ... የበጀት አመቱን እቅድ ለማሳካት ቁልፍ ሚና ከሚኖራቸው ዝግጅቶች መካከል አንዱ የሆነው የፕሮጀክቱን የሰው ሃይል በአመለካካትና በክህሎት ማብቃት መሆኑን ዋና ስራ አስኪያጁ ጠቁመው 139 የፕሮጀክቱ ስራ አመራሮችና ሠራተኞች በውጪ አገር፣ በኮርፖሬሽኑና በፕሮጀክት ደረጃ በተለያዩ ርዕሶች ስልጠና እንዲያገኙ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡ በፕሮጀክቱ በመካሄድ ላይ የሚገኘው ልማት ለአካባቢውና ለአገሪቱ ምጣኔ ሐብት እድገት ሊኖረው በሚችለው ጠቀሜታ 12 ዙሪያ ለአካባቢው ህብረተሰብ ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸው ስራውን ከዞን፣ ከወረዳና ከቀበሌ አመራሮች ለመጀመር አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡ በተያያዘም ለልማቱ ከሚፈለገው መሬት ላይ ተነሺ ለሆኑ ዜጎች የማህበራዊ ተቋማት ግንባታ ለማስፈጸም ከአካባቢው የአስተዳደር አካላት ጋር በመሆን እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሚገኝ ዋና ስራ አስኪያጁ አመልክተዋል፡፡
  • 13. በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና ድጋፍ ፈንድ አቋቋሙ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በደማቸው የሚገኝባቸውን ሠራተኞችና ወላጆቻቸውን በበሽታው ያጡ ህጻናትን በቋሚነት ለመርዳት የሚያስችል የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና ድጋፍ ፈንድ አቋቋሙ፡፡ በዚሁ ወቅት የስኳር ኮርፖሬሽን ኤች.አይ.ቪ ኤድስ መከላከያ አስተባባሪ ወ/ሮ ካሰች ሺበሺ በፋብሪካው ያለውን የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ስርጭትና የመከላከል ስራውን በተመለከተ የዳሰሳ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡ ፋብሪካው ዕለቱን ምክንያት በማድረግ የድጋፍ ፈንዱ የተቋቋመው የኤች.አይ.ቪ/ በሠራተኞች መዝናኛ ክበብ ባካሄደው ልዩ ኤድስ ቀን ታህሳስ 5 ቀን 2006 ዓ.ም ዝግጅት በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ወላጆቻቸውን በፋብሪካ ደረጃ በተከበረበት ወቅት ላጡ 46 ታዳጊ ህጻናት የ13 ሺ 8ዐዐ ብር የድርጅቱ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ድጋፍ አድርጓል፡፡ ባደረጉት ውይይት ላይ በተደረሰ ስምምነት ነው፡፡ በዝግጅቱ ላይ የፋብሪካው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጨምሮ ሠራተኞች፣ የስኳር በስምምነቱ መሰረት ሰራተኞቹ በየወሩ ኮርፖሬሽን ተወካዮችና የምሥራቅ ሸዋ ጤና በቋሚነት ከወር ደመወዛቸው ብር 0.5 ቢሮ ተወካይ ተገኝተዋል፡፡ በመቶ ለመከላከልና ድጋፍ ስራው እንዲውል ተስማምተዋል፡፡ በፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ቀደም ሲል በሥነ ሥርዓቱ ላይ የወንጂ ሸዋ ስኳር የተቋቋመው የኤች. አይ.ቪ ኤድስ ፈንድ ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አታክልቲ ለ20 በበሽታው ወላጆቻቸውን ላጡ ህጻናት ተስፋይ የፋብሪካው ሰራተኞች በራሳቸው በየወሩ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተነሳሽነት ቋሚ የኤች አይ ቪ ኤድስ ድጋፍና ይታወቃል፡፡ የፈንዱ የገቢ ምንጭ መከላከል ፈንድ ለማቋቋም በመቻላቸው የሰራተኛው መዋጮና ከፋብሪካው በየአመቱ ልባዊ ምሥጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ የሚመደብ ገንዘብ መሆኑ ይታወሳል፡፡ የፋብሪካው ሰራተኞች ፈንዱን ለማቋቋም ቁርጠኝነታቸውን አሳይተዋል 13
  • 14. ጣፋጭ ዜና መፅሄት የፋብሪካው ሴት ሰራተኞች በለውጥ ንቅናቄ ግንባር ቀደም ሚና እንጫወታለን አሉ ዘመቻው ላይ በመሳተፍ የሰራተኞቹን የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሴት ሠራተኞች በፋብሪካው ዓላማ አበረታተዋል፡፡ በተጀመረው አጠቃላይ የለውጥ ንቅናቄ ግንባር ቀደም ሚና እንደሚጫወቱ አስታወቁ፡፡ በጽዳት ዘመቻው ማጠቃለያ ሥነስርዓት ላይ ሁለቱም የሥራ ኃላፊዎች ‹‹በሴቶች የነቃ ተሳትፎ ምርታማነታችንን እናሳድጋለን›› ባስተላለፉት መልዕክት ከዚህ ቀደም በሚል መሪ ቃል 220 የሚሆኑ የፋብሪካው ሴት የነበረውን የተዛባ የሥርዓተ-ፆታ ሠራተኞች ህዳር 1/2ዐዐ6 ዓ.ም በፋብሪካው የምርት ቦታ አመለካከት በመለወጥ ሴቶችንና ወንዶችን በመገኘት የጽዳት ዘመቻ ያካሄዱ ሲሆን፣ ያከናወኑት በሁሉም ዘርፍ እኩል ተሣታፊና ተጠቃሚ ተግባር በገንዘብ ሲተመን ከ 8 ሺህ ብር በላይ መሆኑ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት በአጭር ጊዜ ታውቋል፡፡ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል ብለዋል፡፡ የስኳር ኮርፖሬሽን ሥርዓተ-ፆታ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሴቶች አካባቢንና ማህበረሰብን ወደ እንጉዳይ አሰፋ እንዲሁም የኮርፖሬሽኑ የኤች.አይ.ቪ./ መልካምና ወደ ምርታማነት የመለወጥ ኤድስ መከላከያ አስተባባሪ ወ/ሮ ካሰች ሺበሺ በጽዳት አቅም ያላቸው መሆኑን በመገንዘብ የሴት ሰራተኞቹ የጽዳት ዘመቻ ከ 8 ሺ ብር የፋብሪካው ሴት ሰራተኞች የጀመሩትን በላይ የሚገመት ገንዘብ አድኗል አርዓያነት ያለው ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉም አሳስበዋል፡፡ የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘነበ ይማም በወቅቱ ባደረጉት ንግግር የፋብሪካውን ምርታማነት ለማሳደግ እየተካሄደ ባለው አጠቃላይ የለውጥ ንቅናቄ ውስጥ ሴት ሠራተኞች የጀመሩትን ብርቱ ጥረት አጠናክረው እንደሚቀጥሉና ፋብሪካውም በዚህ አመት 1.3 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ለማምረት የያዘው ዕቅድ እንደሚሳካ ያላቸውን ሙሉ እምነት ገልጸዋል፡፡ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የሥርዓተ ፆታ ቡድን መሪ ወ/ሮ ዓለሚቱ ጉልቴ በበኩላቸው የጽዳት መርሃ ግብሩ ዋና አላማ ሴት ሰራተኞች ለፋብሪካው ምርታማነትና እድገት ሊያከናውኗቸው ከሚችሉት በርካታ ተግባራት ውስጥ የፋብሪካውን የምርት ቦታ ጽዱ በማድረግ ለስራ አመቺና ማራኪ የሚሆንበትን ሁኔታ መፍጠር ነው ብለዋል፡፡ 14
  • 15. በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ የስኳር ልማት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች የልማቱ ተዋናዮች እየሆኑ ነው የስኳር ልማት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች የስኳር ልማቱን እንደሚፈልጉ ከመግለፅ ባለፈ የልማቱ ተዋናዮች እየሆኑ እንደሚገኙ ተገለጸ፡፡ የስኳር ኮርፖሬሽን የሕዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳመነ ዳሮታ ከዜና መጽሔቱ ዝግጅት ክፍል ጋር ባደረጉት ቆይታ የስኳር ልማት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ልማቱን እንደሚፈልጉት ከመግለጽ ባለፈ ቀዳሚ ተዋናዮች እየሆኑ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ መንግስት ከፍተኛ ወጪ በማውጣት እያከናወነ የሚገኘው የስኳር ልማት ልማቱ የሚካሄድበትን አካባቢ ህብረተሰብ ይሁንታ ካላገኘ ዋጋ እንደማይኖረው ይገነዘባል ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በዚህ ረገድ በልማቱ አጠቃላይ ሂደት ላይ በመወያየትና በመተማመን እየሠሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ በዋናነት ልማቱ የሚከናወንበት አካባቢ ሕብረተሰብ ከልማቱ ተጠቃሚ የሚሆንበትን ስልት በመንደፍ ነው ያሉት አቶ ዳመነ ይህም እስካሁን በተከናወኑ ሥራዎች በተግባር መረጋገጡን አብራርተዋል፡፡ ሕብረተሰቡ የስኳር ልማቱ የራሱ መሆኑን በመገንዘቡና በማመኑ በአንዳንድ ቦታዎች “በነጻ የሸንኮራ አገዳ ለምን አንተክልም?” በማለት ከመጠየቅ ባለፈ በበለስ የስኳር ልማት ፕጀክት የሸንኮራ አገዳ በመትከል የልማቱ አጋር መሆኑን በተግባር እያሳየ ይገኛል ብለዋል፡፡ መንግስት የስኳር ልማቱን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አካል ሲያደርግ የስራ እድል ፈጠራን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ በ2005 ዓ.ም በነባር ስኳር ፋብሪካዎችና በፕሮጀክቶች ለ60 ሺህ ዜጎች የስራ እድል እንደተፈጠራላቸው ገልፀው ይህ ጥረት ወደፊትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ ከአቶ ዳመነ ዳሮታ ጋር የተደረገው ሙሉ ቃለ ምልልስ በገጽ 16 ተስተናግዷል፡፡ የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች የብሔር ብሐረሰቦችና ሕዝቦች ቀን... የተዛቡ ግኝኙነቶችን በማረም የሕገ መንግስታዊ ስርአቱ አደጋ የሆኑትን የሃይማኖት አክራሪነትንና ኪራይ ሰብሳቢነት መታገል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ አያይዘውም በስኳር ልማት ዘርፍ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የተቀመጡትን ግቦች እውን ለማድረግ የዋናው መስሪያ ቤት፣ የፋብሪካዎችና የፕሮጀክቶች ሠራተኞች በህብረት በመስራት የሕገ መንግስቱን ዓላማዎች ማሳካት እንደሚጠበቅባቸው አመልክተዋል፡፡ ሕገ መንግስቱ የፀደቀበትን ቀን ማክበር ሠራተኞች እርስ በርሳቸው እንዲተዋወቁ ያስችላል ያሉት አማካሪው ሕገ መንግስቱን ተከትለው ከወጡ የልማት እቅዶች መካከል አንዱ የሆነውን የስኳር ልማት ዘርፍ ስኬትን ለማረጋገጥ የኮርፖሬሽኑ አመራርና ሰራተኛ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ጥረት ማድረግ እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋል፡፡ በቀጣይም አንድ ጠንካራ የፖለቲካና የምጣኔ ሐብት ማሕበረሰብ ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች የዘርፉን እቅዶች ለማሳካት በትጋት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በእለቱ «የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስትና ሕብረ ብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓት « በሚል ርእስ የመነሻ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ሕገ መንግስቱን የተመለከቱ የጥያቄና መልስ ውድድሮችም ተካሂደዋል፡፡ ይህ የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በስኳር ፋብሪካዎችና በፕሮጄክቶችም በድምቀት ተከብሯል፡፡ በተያያዘም የዓለም ኤድስ ቀንና የነጭ ሪቫን ቀን በዕለቱ በኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ታስቦ ውሏል፡፡ የበዓሉ ታዳሚዎች 15
  • 16. ጣፋጭ ዜና መፅሄት በኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየሦስት ወሩ እየታተመ የሚወጣው ጣፋጭ ዜና መጽሔት በዚህ ወር ዕትሙ የስኳር ልማት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚኖረው ህዝብ የልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆን እየተከናወኑ ስላሉ ሥራዎች እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ከስኳር ኮርፖሬሽን የሕዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳመነ ዳሮታ ጋር ያደረገው ቆይታ እንደሚከተለው ቀርቧል ፡፡ ጣፋጭ- በያዝነው በጀት ዓመት በመንደፍ ነው፡፡ በመሆኑም እስከ አሁን የጤና ተቋማት፣ የአርሶ አደር ማሰልጠኛ የዘርፉ ዋነኛ የሥራ ትኩረት ምን በበለስ ስኳር ልማት አካባቢ በአማራ ክልል ማዕከላት፣ የቀበሌ ጽ/ቤቶች፣ የፖሊስ በጃዊ ወረዳ በሁለት ሠፈራ ጣቢያዎች ጣቢያዎች፣ የውሃ ተቋማት፣ መዳረሻ እንደሆነ ቢገልጹልን? (አሊኩራንድና ኩምብር)፣ በቤኒሻንጉል መንገዶች እና መሰል ማህበራዊ ተቋማት አቶ ዳመነ - ኮርፖሬሽኑ የስኳር ምርት ጉሙዝ ክልል በፓዌና ዳንጉር ወረዳዎች እየተገነቡና የተጠናቀቁት አገልግሎት ከውጪ ማስገባትን በማስቀረት የአገር በሁለት ሠፈራ ጣቢያዎች (አባወሬኛና እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ውስጥ ፍጆታን ከማሟላት ባሻገር ወደ ባንባጅዋ) እና በወልቃይት በቆራሪት ሠፈራ እንዲሁም በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ውጪ አገር ኤክስፖርት ለማድረግ ጣቢያ መልሰው ለሚቋቋሙ የህብረተሰብ ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ያለውን ጥረት ክፍሎች አገልግሎት የሚሰጡ ት/ቤቶች፣ አካባቢ በቦዲ ሦስት መንደሮች፣ በጉራ ውጤታማ ለማድረግ የኢንዱስትሪ አካባቢ ሠላም መሆን ወሳኝ ነው፡፡ ስለሆነም የዘርፉ የበጀት ዓመቱ የትኩረት አቶ ዳመነ ዳሮታ በስኳር ኮርፖሬሽን የሕዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቅጣጫ የኮርፖሬሽኑ የልማት ዕቅድ ተፈፃሚ እንዲሆን የበኩሉን ድርሻ መወጣትና በሂደትም በልማት አካባቢው የሚገኝ ህብረተሰብ ከልማቱ ተጨባጭ ተጠቃሚነቱን እያረጋገጠ እንዲሄድ ከክልል መንግስታት ጋር በቅንጅት መሥራት ነው፡፡ ጣፋጭበስኳር ፋብሪካዎችና ኘሮጀክቶች አካባቢ የሚገኘው ህብረተሰብ የልማቱ ዋንኛ ተጠቃሚ እንዲሆን እስካሁን የተከናወኑ ሥራዎችን (ከማህበራዊ አገልግሎቶችና ከመሰረተ ልማት ግንባታ፣ ከሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ከሥልጠና ….. አኳያ ) ጠቅለል አድርገው ቢያብራሩልን? አቶ ዳመነ - መንግስት የስኳር ልማትን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አካል ሲያደርግ በዋነኝነት ልማቱ የሚከናወንበት አካባቢ ህብረተሰብ ከልማቱ ተጠቃሚ የሚሆንበትን ስልት 16
  • 17. በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ አንድ መንደርና በሃይለ ውሃ ሁለት መንደሮች በአጠቃላይ በስድስት መንደሮች በእያንዳንዳቸው ከአስር በላይ ማህበራዊ ተቋማትና የመሠረተ ልማት አውታሮች እየተገነቡ ያለበት ሁኔታ ሲኖር የቦዲ ሦስት መንደሮች ተጠናቀው ለአርብቶ አደሮች አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ከዚህም ሌላ በኮርፖሬሽኑ እና በደቡብ ብ/ብ/ እና ሕዝቦች ክልል የጋራ በጀት በማኪ ወንዝ አካባቢ በአንድ መንደርና በሻርማ ወንዝ አካባቢ በሁለት መንደሮች አርብቶ አደሮች ቀደም ሲል በሚኖሩበት አካባቢ የውሃ አማራጭ በመገኘቱ ባሉበት አገልግሎት እንዲያገኙ የማህበራዊ ተቋማትና የመሠረተ ልማት አውታሮች እየተገነቡ ናቸው፡፡ (TVET) ጋር በመቀናጀት በኮርፖሬሽኑ ሙሉ ወጪ የመለስተኛ ሙያ ስልጠና እንዲያገኙ እየተደረገ ይገኛል፡፡ በዚህ መሰረት በኩራዝ 232፣ በበለስ 79 እና በወልቃይት 204 ወጣቶች በተለያዩ የኮንስትራክሽን ሙያዎችና በትራክተር ኦፕሬተርነት ስልጠና አግኝተው በፕሮጀክቶቹ እንዲቀጠሩ ተደርጓል፡፡ ይህ ወደፊትም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ ጣፋጭ- ከካሳ ክፍያ፣ ከመልሶ ማቋቋም (መንደር ማሰባሰብ፣ ሰፈራ) እና በመስኖ ከሚለማ መሬት ርክክብ ሥራዎች ጋር በተያያዘ የተከናወኑ ተግባራትን ቢገልጹልን? በዚህ ረገድ አልፎ አልፎ ከህብረተሰቡ የሚቀርቡ ቅሬታዎች በምን አግባብ በፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ይዞታ ውስጥ እየተፈቱ ነው? ህጋዊ መሠረት ሳይኖራቸው ለረጅም ጊዜ የቆዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ከፋብሪካው አቶ ዳመነ -የሀብት ቆጠራና ካሳ ክፍያም አስተዳደር ወሰን ውጪ ለማስፈር በአዲሱ ሆነ ዜጎችን መልሶ ማቋቋም ስራዎችን የሰፈራ ጣቢያ ከስምንት በላይ ማህበራዊ የምናከናውነው ልማቱ ከሚገኝበት ተቋማት እየተገነቡ ሲሆን፤ በአርጆ ክልል ጋር በመቀናጀት ነው፡፡ ዲዴሳ፣ በወንጂ ሸዋ እና በመተሐራ ስኳር በመሆኑም እስከ አሁን ባለው ሂደት የጎላ ፋብሪካዎች አካባቢ ለሚገኙ የህብረተሰብ ችግር አላጋጠመንም ብሎ መውሰድ ክፍሎች አገልግሎት የሚሰጡ ማህበራዊ ይቻላል፡፡ በበለስና በወልቃይት ስኳር ተቋማትን ለመገንባት እየተንቀሳቀስን ልማቶች ምክንያት መልሰው የሚሰፍሩ እንገኛለን፡፡ ዜጎች በአዋጁ መሠረት ሀብትና ንብረት ተገምቶ ካሳ እንዲከፈላቸው እየተደረገ በሌላም በኩል በውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ነው፡፡ ሚኒስቴር ባለቤትነት በተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ አካባቢ ለሚገኙ አርብቶ አደሮች በኩራዝ አካባቢ የሚገኘው መሬት ቀደም በዱብቲ ወረዳ በአስር መንደሮች ሲል በአርብቶ አደሮች ተይዞ በቋሚነት በእያንዳንዳቸው የሰባት ማህበራዊ የለማ ንብረትና ሀብት የሌለ በመሆኑ ተቋማት ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን፣ እስከ አሁን ድረስ የካሳ ክፍያ ያልተፈፀመ ተቋማቱ በከፊል አገልግሎት እየሰጡ ቢሆንም የአርብቶ አደሩን ኑሮ በዘላቂነት ይገኛሉ፡፡ በከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክት ለመለወጥ መንግስት ከፍተኛ ወጪ አካባቢም ለሚገኙ አርብቶ አደሮች በማውጣት የመስኖ መሰረተ ልማት ተመሳሳይ አገልግሎት እንዲያገኙ እየተሰራ በመስራት አርብቶ አደሩ ተጠቃሚ ነው፡፡ እንዲሆን እየሰራ ይገኛል፡፡ በተንዳሆና በከሰምም በመንግስት ከፍተኛ ወጪ ከስራ ዕድል ፈጠራ አንፃር በነባር የመስኖ መሰረተ ልማት ለአካባቢው ስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች አርብቶ አደሮች እየተገነባ ይገኛል፡፡ በ2005 ዓ.ም ወደ 60 ሺህ የስራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ጣፋጭየስኳር ልማት ዘመን መጨረሻ በዘርፉ ከ200 ሺህ በላይ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ይፈጠራል፡፡ የህዝብ ንቅናቄ በመፍጠር ህዝቡ በተለይ በልማቱ አካባቢ የሚኖሩ ዜጎች በባለቤትነት ስሜት ተነሳስቶ የልማቱ በሚፈጠሩ የስራ ዕድሎች ይበልጥ አጋዥ ኃይል እንዲሆን እየተከናወኑ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ከቴክኒክና የሚገኙ ሥራዎችን ቢያብራሩልን ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ፡፡ ምንስ ውጤት ተገኝቷል? አቶ ዳመነ - ምንም እንኳ መንግስት ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ለአገርና ልማቱ ለሚከናወንበት አካባቢ የጎላ ጠቀሜታ ያለው ልማት እያከናወነ ቢሆንም ህብረተሰቡ ሳያምንበት በጫና የሚፈፀም ልማት ዋጋ የማይኖረው መሆኑን ከማንም ይልቅ ይገነዘባል፡፡ በመሆኑም ወደ የትኛውም ስራ ከመግባታችን በፊት ስለልማቱ አጠቃላይ ሂደት ከህብረተሰቡ ጋር በመወያየትና በመተማመን እየሄድን እንገኛለን፡፡ ውጤቱንም ስንመለከት በልማቱ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ልማቱን እንደሚፈልጉ ከመግለፅ ባለፈ የልማቱ ቀዳሚ ተዋናዮች እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ በአንዳንድ ቦታዎችም የሸንኮራ አገዳ ተከላ ሳይቀር “ በነፃ ለምን አንተክልም” ከማለት ባለፈ በበለስ የስኳር ልማት ፕሮጀክት የሸንኮራ አገዳ በመትከል አጋርነታቸውን እየገለጹ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ የገባኸውን ቃል ወደ ተግባር መለወጥ እስከ ቻልክ ድረስ ህብረተሰቡ ከልማት ፍላጎት ባለፈ የባለቤትነት ስሜት እያደረበት ይሄዳል፤ አሁንም እየታየ ያለው ይህ ነው፡፡ ጣፋጭ- የሸንኮራ አገዳ አብቃዮችን እና አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማትን በማደራጀት፣ በማስተባበርና በመከታተል ረገድ ምን ያህል ርቀት ተጉዛችኋል? የሥራችሁን መገለጫዎች ቢጠቅሱልን? አቶ ዳመነ - እንደሚታወቀው የሸንኮራ አብቃይ አርሶ አደሮች የህብረት ስራ ማህበራት ልምድ ያለው በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ነው፡፡ የማደራጀት ስራው የሚሰራው ከማህበራት ማደራጃ ጽ/ቤቶች ጋር በመቀናጀት ሲሆን አርሶ አደሩ ከመሬት ይዞታው ሳይፈናቀል የልማቱ ቀኝ እጅ በመሆን ሸንኮራ እያመረተ ለፋብሪካው እንዲያቀርብ እና ተጠቃሚ እንዲሆን እየተደረገ ይገኛል፡፡ በዚህ ሂደት እስከ አሁን 31 መሠረታዊ የህብረት ስራ ማህበራት እና አንድ ዩኒየን የተቋቋሙ ሲሆን በልማቱ ዙሪያ ያሉ ችግሮችና የመፍትሄ አቅጣጫን በተመለከተ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ዝርዝር ጥናት በማጥናትና ከአርሶ አደሩ ጋር በመተማመን በየጊዜው »» ገጽ.18 17
  • 18. ጣፋጭ ዜና መፅሄት እኛ የምንሰራው ለህዝብ ነው፤ ህዝቡ ያላመነበትና ተጠቃሚ የማይሆንበትን ልማት አንሰራም ” የሚያጋጥሙትን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ስራ ገብተናል፡፡ መለወጥ የማይፈልጉ አካላት የሐሰት ውንጀላ ነው፡፡ በሌላ በኩል በተለይ በአዳዲስ ፕሮጀክቶች አካባቢ የጥቃቅንና አነስተኛ አንቀሳቃሾች የስራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው ከሚመለከታቸው የመስተዳድር አካላት ጋር እየሰራን በመሆኑ ብዙ ወጣቶችና ሴቶች ተጠቃሚ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ ይልቁንም አርብቶ አደሩ በልማት ክልሉ ውስጥ የአኗኗር ባህሉና ወጉ ሳይዛባ በመንደር እየተሰባሰበ ውሃን ማዕከል ያደረገ የመስኖ መሠረተ ልማት የሚሰጠውና የማህበራዊ ተቋማት የሚገነቡለት በመሆኑ ሌሎች ይህንን ለውጥ እያዩ ለምን ፈጥናችሁ ወደ እኛም አትመጡም እያሉን ነው ፡፡ ጣፋጭ - ልማቱን ከማፋጠን አንጻር ከክልሎች ፣ ከዞኖች ከወረዳዎችና ከሌሎች የባለ ድርሻ አካላት ጋር ያላችሁ ግንንኙነት ምን ይመስላል? አቶ ዳመነ - የእኛ ስራ ከህዝብ ጋር በቀጥታ የተገናኘ እንደመሆኑ መጠን ልማቱ ከሚገኝባቸው ክልሎች ጋር በቅርበት የምንሰራ ሲሆን ክልሎች የስኳር ልማት ስቲሪንግ ኮሚቴ በማዋቀር ለስራው ትኩረት በመስጠት በባለቤትነት እየመሩት ይገኛሉ፡፡ እስከ አሁን ያለን ግንኙነት መልካም የሚባል ነው፡፡ እንዲሁም በአርሶ አደር አካባቢዎች ተገቢው ካሳ የሚከፈልና መሟላት ያለበት ማህበራዊ ተቋምና የመሠረተ ልማት አውታሮች ከነበረው ተመጣጣኝና በተሻለ ሁኔታ እየተገነባ ነው፡፡ የተለያዩ የስራ ዕድሎች እየተፈጠሩ በመሆናቸው ተነሺው ህብረተሰብ በተጨባጭ ተጠቃሚ መሆኑን ስለተገነዘበ የልማቱ አጋር እየሆነ ይገኛል፡፡ በሌላ በኩል የሸንኮራ አገዳ ልማት የአረንጓዴ ልማት አካል እንደመሆኑ መጠን የአካባቢ ጣፋጭ- «በስኳር ልማት ሳቢያ ህዝብ አየር ንብረት በመጠበቅ አዎንታዊ የሆነ ተፈናቀለ፣ ሰብዓዊ መብቱ ተጣሰ፣ ሚናን ይጫወታል፡፡ ከእምነት ቦታ አንፃርም ለዜጎች ተገቢው ካሳ አልተከፈለም፣ በአንዳንድ የውጪ ሚዲያ ሳይቀር ብዙ ሲባል ደን ተመነጠረ፣ ቅርሶች አልተጠበቁም፣ የነበረው የዋልድባ ገዳም ተደፈረ የሚል የእምነት ቦታ ተደፈረ.» የሚሉ ነበር፡፡ ልማቱ በገዳሙ ላይ የሚያመጣው ተደጋጋሚ ስሞታዎች (በተለይም ተፅዕኖ የሌለ ቢሆንም አንዳንድ የተለየ ፍላጎት ደግሞ የኩራዝ ስኳር ልማት ኘሮጀክት ያላቸው አካላት አጀንዳ ለማድረግ በሰፊው በሚካሄድበት አካባቢ) የሰብዓዊ ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ሆኖም በአካባቢው ያለው መብትና የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋች ነን ህብረተሰብ ሁኔታውን በቅርበት የሚያውቀውና በሚሉ ተቋማትና በአንዳንድ የውጭ የሚገነዘበው በመሆኑ ለልማቱ ያለውን አጋርነት ሚዲያዎች ይናፈሳሉ፡፡ በዚህ ላይ እየገለፀ ይገኛል፡፡ የእርስዎ ምላሽ ምንድ ነው? በአሁኑ ጊዜ በተሳሳተ አቅጣጫ ሲጓዙ የነበሩ አቶ ዳመነ - በየጊዜው በተለያዩ ፍትሐዊነት ጭምር ስህተት መሆኑን በማመን ከመንግሥትና በጎደላቸው ተቋማት የሚናፈሱ አሉባልታዎችና ከሕዝብ ጎን በመቆም ልማቱን ለመደገፍ ጥያቄ ተጨባጭ እውነታውን ስንመለከተው እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ በአጠቃላይ በሁሉም የማይገናኝበት ሁኔታ ነው ያለው፡ አካባቢ ያለው ህዝባችን የልማቱን ፋይዳ ፡ እኛ የምንሰራው ለህዝብ ነው፤ ህዝቡ በመገንዘብ የራሱን አስተዋፅዖ እያበረከተ የሚገኝ ያላመነበትና ተጠቃሚ የማይሆንበትን ልማት በመሆኑ የሰብዓዊ መብትና የአካባቢ ጥበቃ አንሰራም፡፡ በደቡብ ኦሞ መንግስት ህዝቡን ተሟጋች ነን የሚሉ አካላት ይህንኑ በማመን በኃይል እያፈናቀለ መሆኑን የሚናገሩ አሉ ከአፍራሽ ቅስቀሳቸው ቢቆጠቡ መልካም ነው ፡፡ ይህ ከእውነት የራቀ እና የአርብቶ አደሩን እላለሁ፡፡ 18
  • 19. ጣና በለስ እናስተዋውቃችሁ የተቀናጀ የስኳር ልማት ፕሮጀክት ከአምስት አመታት በፊት በ2001 ዓ.ም ነበር በአማራ ብሔራዊ ክልል «ጣና የተቀናጀ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት» የተጀመረው፡፡ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በተጠነሰሰበት በ2003 ዓ.ም የአካባቢውን እምቅ አቅም እንዲሁም አዋጭነቱን ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚኒስትሮች ምክር ቤት በደንብ ቁጥር 192/2003 ፕሮጀክቱ «ጣና በለስ የተቀናጀ ስኳር ልማት ፕሮጀክት» በሚል ስያሜ በስኳር ኮርፖሬሽን ስር እንዲሆን አደረገው፡፡ ከዚህ ጊዜ አንስቶ ፕሮጀክቱን እውን ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ነው፡ ፡ የወንዙን አቅጣጫ በማስቀየር የተሰራውና 13 ሜትር ቁመትና በሰከንድ 60 ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ የመልቀቅ አቅም ያላቸው ስድስት በሮችን ያካተተው ዘመናዊ የውሃ መቀልበሻ አናት (ዊር) የሰሜን ጎንደሩ አለፋ ወረዳ ፣ የምዕራብ ጎጃሙ ደቡብ አቸነፈርና የአዊ ዞኑ ጃዊ ወረዳዎች በሚዋሰኑበት ስፍራ ላይ ይገኛል፡፡ ውሃው ወደ እርሻ ማሳዎች እንዲደርስ ለማድረግም 31 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ዋና ካናል ተገንብቷል፡፡ በፕሮጀክቱ የእስከአሁን እንቅስቃሴ ከ17,ዐዐዐ ሄክታር በላይ መሬት ከሦስተኛ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ወገን ነፃ በማድረግ ለአገዳ እርሻ ዝግጁ በአዊ ዞን በጃዊ ወረዳ እንዲሁም ከመደረጉም በላይ ውሃ ወደ አገዳ እርሻ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ ለማሰራጨት ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡ መንግሥት በመተከል ዞን በፖዊና ዳንጉር እስከ ህዳር 2006 ዓ.ም አጋማሽ ድረስ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኘው የጣና በለስ 2,724 ሔክታር መሬት ሙሉ በሙሉ የተቀናጀ የስኳር ልማት ፕሮጀክት በሸንኮራ አገዳ ዘር በመሸፈን ለሚገነቡ የጃዊ ፣ ፓዊና ዳንጉር ሜዳዎችን ፋብሪካዎች የሙከራ ተግባርና የዘር ተንተርሶ የሚፈሰውን የበለስ ወንዝን አቅርቦት በራሱ በፕሮጀክቱ እየተሸፈነ አቅጣጫ በማስቀየር 75 ሺ ሄክታር ይገኛል፡፡ መሬት (50ሺህ ሄክታር በአማራ ክልል እንዲሁም 25ሺህ ሄክታር በቤኒሻንጉል የበለስ የተቀናጀ የስኳር ልማት ክልል) ላይ የሸንኮራ አገዳና ሌሎች ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ እያንዳንቸው በቀን ተፈላጊ ሰብሎችን እንዲያመርት ታስቦ 12 ሺ ቶን የሸንኮራ አገዳ የመፍጨት የተጀመረ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው፡፡ አቅም ያላቸው ሦስት ፋብሪካዎች / በለስ ቁጥር 1፣ በለስ ቁጥር 2 እና አይማ ፕሮጀክቱ ከአዲስ አበባ በዳንግላ ፋብሪካ/ ይኖሩታል፡፡ በ75 ሺህ ሄክታር መስመር 558 ኪ.ሜ ወይም በሌላኛው መሬት ላይ የሚለማን ሸንኮራ አገዳ አማራጭ መንገድ ከአዲስ አበባ በግብአትነት የሚጠቀሙት እነዚህ በኮሶበር ቻግኒ 597 ኪ.ሜ ላይ ይገኛል፡ ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው ማምረት ፡ የፕሮጀክቱ ዋና ጽ/ቤት «መለስ ዜናዊ ሲጀምሩ በድምሩ በዓመት 726ሺህ ቶን ጠቅላይ ሰፈር» ከጃዊ ወረዳ ዋና ከተማ ወይም 7 ሚሊዮን 260 ሺህ ኩንታል ፈንደቃ በአንድ ኪ.ሜ ርቀት ላይ ስኳር የማምረት አቅም ይኖራቸዋል። በሚገኝ ቆላማ የአየር ንብረት ባለው ከዚህ በተጨማሪ ከስኳር ተረፈ ምርት አካባቢ የከተመ ነው፡፡ በአመት 62.4 ሚሊዮን ሊትር ኢታኖል እና 165 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ፕሮጀክቱ ለመስኖ ስራ የሚጠቀምበትን እንደሚያመርቱም ይጠበቃል፡፡ ይህም የበለስ ወንዝን አቅጣጫ የማስቀየር አገራችን ተግባራዊ በማድረግ ከዓለም ስራ ሙሉ ለሙሉ የተከናወነው ግንባር ቀደም የሆነችበትን የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂን በመደገፍ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ዓላማዬ ብሎ ከያዛቸው ዋና ዋና ተግባራት አንዱ ለዜጐች የሥራ እድል ፈጠራን ማመቻቸት ነው፡ ፡ በዚህም መሠረት በአሁኑ ጊዜ ለ1ዐ ሺ 6ዐ3 ወንዶችና ለ3ሺ742 ሴቶች በአጠቃላይ ለ14ሺ345 የአካባቢው ነዋሪዎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ እድል ፈጥሮላቸዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅም ከ69 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል እንደሚፈጥር ይጠበቃል፡፡ በ2ዐዐ4 ዓ.ም ፕሮጀክቱ በሚገነባበት አካባቢ ይኖሩ ለነበሩና እንዲሰፍሩ ለተደረጉ 1,909 የጃዊ ወረዳ የቤተሰብ ኃላፊዎች የመኖሪያና የእርሻ ቦታ ከመመቻቸቱም ባሻገር 53 ሚሊዮን ብር የካሣ ክፍያ ተሰጥቶ በአግባቡ በተመረጠላቸው ቦታ ሰፍረው የተረጋጋ ኑሮ በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ነዋሪዎቹ በሰፈሩባቸው አካባቢዎች ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶች ፣ የሰውና የእንስሳት ጤና ኬላዎች ፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተቋማት ፣ ክረምትና በጋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መንገድ በከፍተኛ ወጪ ተገንብተው የአገልግሎቶቹ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ ለስኳር ልማቱ መፋጠን አስተዋጽኦ ለማድረግ በፈቃዳቸው መኖሪያ አካባቢያቸውን እና የእርሻ መሬታቸውን ትተው ከተነሱ የአካባቢው ማሕበረሰብ ልጆች ውስጥ 1ዐኛ ክፍልን አጠናቀው ስራ አጥ የነበሩ 30 ወጣቶችን በመመልመል በጫንጮ ትራክተር ኦፕሬተር ማሰልጠኛ ለሦስት ወር እንዲሰለጥኑ ተደርጎ በፕሮጀክቱ በቋሚ ሠራተኛነት ተቀጥረዋል፡፡ በዚህም ፕሮጀክቱ ለህብረተሰቡ ያለውን አጋርነት በተግባር አስመስክሯል፡፡ 19
  • 20. ጣፋጭ ዜና መጽሔት በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽኝ ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት www.etsugar.gov.et :+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 A.A etsugar@hotmail.com www.facebook.com/etsugar